LYRIC

ላገኛት ነው ዛሬ አፌ ከተፈታ
ካጠገቧ ስደርስ ካልገታኝ ውበቷ
ከራሴው አንደበት ብትሰማኝ ጓግታ
እየወደደችኝ አለች ቃል ሰስታ
2X
ትወጂኛለሽ አውቃለው አይንሽ ይናገራል
እወድሻለው ታውቂያለሽ አይኔ ይናገራል
2X
ወድሻለው ብዬ በአፌ ሳልናገር
ከአፌ ላይ ካወቅሽው የልቤን ቁም ነገር
የሴትነት ወጉ ከፍቅር አይበልጥም
ቃል ከስሜት በላይ ሚዛን ደፍቶ አያውቅም
እየተያየን ስንፈራራ
ስሜታችንን በግልጽ ሳናወራ
አንቺ አንቺ እኔን እኔ አንቺን
እየተጠባበቅን ፍቅራችንን ሳንኖር
2X
ትወጂኛለሽ አውቃለው አይንሽ ይናገራል
እወድሻለው ታውቂያለሽ አይኔ ይናገራል
አይናፋርነቴ ጎልቶ ብሶብኛል
ምን ሚወራ ቀርቶኛል ምን ቢወራ ታሞ
ፍቅራችን እንዳይቀር በአጭር እንዳንቀጨው
ተይ በአፍላ
ተዋዶ ለመኖር ወግ እንዳይሸፍነው
ደርሶ እንዳይቀላቀል ወሬ አይሆንም ጭንብል ተይ
ወሬ እንዳይሆን ጋርዶት
አቤት ፍርሀት ጋርዶት
ሀሜት
ወሬ
2X
ማንስ ይናገር ማን ያውራ
የልቡ ፍቅር ሳይፈራ
ላንቺ ያለኝን ፍቅር አውቀሽው ስሜቴን
ልትቀርቢው ሲገባ ገፋሽው ሀፍረቴን
ቃል ያውቃል ብለሽ በተስፋ ጠበቅሽኝ
ውስጤን እንድነግርሽ አንደበት አውሺኝ
ትወጂኛለሽ አውቃለው አይንሽ ይናገራል
እወድሻለው ታውቂያለሽ አይኔ ይናገራል
2X

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO