Warning: Creating default object from empty value in /home/ethiolyrics/public_html/wp-content/themes/muusico/framework/admin/ReduxCore/inc/class.redux_filesystem.php on line 29
ብር አምባር – EthioLyrics – Ethiopian Lyrics & Video

LYRIC

ሰማያውው ሰማይ ባንዲራሽን ይዞ
ህዝብሽ ባንቺ ፍቅር አለ ተመርዞ
ባህር አራዊትሽ አዕዋፋትሽ ሁሉ
ለዜግነት ክብርሽ ቀን ሌሊት ያዜማሉ
ኧረ ያንቺስ የጉድ ነው ሀገሬ ያንቺስ የጉድ ነው 2X
ስንት ገዳማት ይጸለይልሻል
አባቶች በሰገል ይለምኑልሻል
ወጣቱ ጎልማሳው ይታገልልሻል
ሴት እናት ህጻናት ይጨነቁልሻል
ጀግንነት ከአባት ነው የወረስነው
ከማይበገር ባለታሪክ ሰው
በቃ ያመኛል ወገን ሲነካ
አንድ ነን በዘር የማንለካ
አትንኩኝ ባይ ክንደ ብርቱ
ብርአምባር ሰበረልሽ
አገሩን አያቅ ማንነቱን
ብርአምባር ሰበረልሽ
ስሙ ጀግና ኢትዮጵያዊ
ብርአምባር ሰበረልሽ
ወንድ ወላድ ነው ሰላማዊ
በ….ትብብር
በወግ እርክክብ ዘመን ተሸጋሪ
ተውልድ የሚያጠግብ ታሪክ እንዲኖረን
ኢትዮጵያዊ የሚል በአለም የሚያኮራ
ስማችንን እንትከል
በሀገራችን ጸንቶ እንዳይኖር መከራ
ይታይ ህዝባዊነት ከአጽናፍ አጽናፍ ይብራ
የጀግና ህዝብ እናት ኩሪ በወለድሽው
ኮከብሽም ይርገፍ አምሮሽ ካላጌጥሽው
መልኬ ኢትዮጵያዊ አጥንት የማይነቃ በሉኝ እኔ እራሴ
ኢትዮጵያ ነኝ በቃ ዘርን በማመንዘር ክፉ እተሰራ
ባይረሳ ምነው የጥንቶቹ አደራ
ተውኝ እተዋለው 6X
ይህቺ የማትረባ ሀገር ብለን በምናየው
ውሸት በነገሩን ባላረጋገጥነው
ስንኮንንሽ ኖረን ቀን ይካስሽ ዛሬ
ለካ ሰው ነው ክፉ አንቺ ደግ ነሽ ሀገሬ
ከማሳው ዘርቶ ማማው ወቶ
የምዬን ማጀት በአግባቡ ሞልቶ
ያገሩን ታሪክ በጥብቅ ሲጠብቅ
ወንድ ሚል ማነው የሚነቀንቅ
ተው ተው ተው
በከተማው ለሀገሩ
ብርአምባር ሰበረልሽ
አልፎ አያውቅም ድንበሩን
ብርአምባር ሰበረልሽ
ደፍሮ የነካት ወየውለት
ብርአምባር ሰበረልሽ
የአለም ንግስት ኢትዮጵያ ናት
ብርአምባር ሰበረልሽ
አ…ልፈራም ከእንግዲህ
አምላክ የማይነሳን የልባችንን አይቶ ነው
ቅሉን የሰጠን አቀባበላችን ያማረ እንደሆነ
አጨራረሳችን ይሁን የሰመረ
ሙስሊም ክርስትያኑ በስምሽ ተነጥፎ
በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለም ተነክሮ ማን ይመልሰዋል
ሚስጥሩ የገባው ጀግና ውለጅ ደግመሽ ምጥሽ ለድህነት ነው
ሙዚቃ እንኳን በቅጥ የሚደመጥበት
ጊዜው ተመለሰ ክብር ይግባው
ያለደም መፋሰስ መኖር እንደሚቻል
እንወቅ ልምድ ይሁነን ይሄም ይወረሳል
ተውኝ እተዋለው 6X
ተው ተው ተው
ያሉህ እንደው ይሄም አሰማ
ተው ተው ተው…….
ሊነጋ ሲል ነው ጨለማ
እኔ ባለሁበት
ለውጥን ተመለከትኩ
የህዝቤን ነጻነት
ምሩቅ ስራ ፈቶ
ወጣት ምላሽ አቶ
በእናት በአባቱ ቤት እድሜው አርባ ሞልቶ
እርጅና እመጣ ለውጥ ሳናመጣ
ተስፋችን ተሟጦ ነበር ስንቀጣ
ኧረረረረረ
ዝም ልል ፈልጌ
ታግሼ ለማየት
አልቻልኩም ልለፍልፍ ሆዴም ቂም ይውጣለት
ውለድ የጀግና አባት ደመረልህ
ጊዜው ካልደረሰ የሚቀነስ የለም
ሺ አመት ላይኖር አንጥፋ ዘላለም
ኧረረረረረ…
በሾ በግፍ በለበሰው ላይ እኛ አንሰራም ግፍ
አንመለስም
ተውኝ እተዋለው

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO