LYRIC

ልንገርሽ ስሚኝ
አሁን ብዙ አሞኛል
ከጎኔ ሳጣሽ በድንገት
እንዴት ስሆን ብታይ
ናፍቆትሽ ብሶ
ሁሉን አስታውሶ
እውነት
2X
ነይልኝ ነይ የደስታ ሚስጥሬ
በፍቅርሽ ተወጣጥሬ
ለሌላ ዝግ ነው በሬ
ነይልኝ ነይ የደስታ ሚስጥሬ
የሚታመመው የሚታከመው
ልቤ በፍቅርሽ ነው
ያንቺ ብቻ ነው ያንቺ ብቻ ነው
ይሄ እውነት ነው እውነት ፍቅር ነው
በዘመን የማይቀየረው
ነይልኝ ነይ የደስታ ሚስጥሬ
በፍቅርሽ ተወጣጥሬ
ለሌላ ዝግ ነው በሬ
ነይልኝ ነይ የደስታ ሚስጥሬ
የሚታመመው የሚታከመው
ልቤ በፍቅርሽ ነው
ጽጌሬዳዬ የእኔ አበባ
የውብ ተፈጥሮሽ መአዛሽ ከኔ አይጠፋም
ጭራሽ በልቤ አዳራሽ
ትልቅ ነው ስፍራሽ
እውነት
2X
ነይልኝ ነይ የደስታ ሚስጥሬ
የሚታመመው የሚታከመው
ልቤ በፍቅርሽ ነው
ያንቺ ብቻ ነው ያንቺ ብቻ ነው
ይሄ እውነት ነው እውነት ፍቅር ነው
በዘመን የማይቀየረው
ነይልኝ ነይ የደስታ ሚስጥሬ
በፍቅርሽ ተወጣጥሬ
ለሌላ ዝግ ነው በሬ
ነይልኝ ነይ የደስታ ሚስጥሬ
የሚታመመው የሚታከመው
ልቤ በፍቅርሽ ነው
ልቤነው ልቤ ልቤ ነው
በፍቅር አንዴ ያመነው
ያንቺ ብቻ ነው ያንቺ ብቻ ነው
ይሄ እውነት ነው እውነት ፍቅር ነው
በዘመን የማይቀየረው
ነይልኝ ነይ የደስታ ሚስጥሬ
በፍቅርሽ ተወጣጥሬ
ለሌላ ዝግ ነው በሬ
ነይልኝ ነይ የደስታ ሚስጥሬ
የሚታመመው የሚታከመው
ልቤ በፍቅርሽ ነው
2X

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO