LYRIC

መሄድሽ ግድ ሆኖ ሆኖ ሳየው
የማይጠግብሽ አይኔ አለቀሰልሽ
በእንባ እርሰሽ ፊትሽ ሳይሽ
አፌ ተሳሰረ እንዴት ላጽናናሽ
ተቃቅፈን ስንላቀቅ ላይቀር መራራቃችን
አቃተኝ ጉልበት አጣሁ ትዝ አለኝ ያ ፍቅራችን
ኧረ እንዴት አሜን ብዬ ልቀበል መራቅሽን
ባዶነት ውስጤን ሞላው ሳስበው መሄድሽን 2X
አትሂጅ እንዳልልሽ በእጄ ምንም የለም
ጨክኜ እንዳልሸኝሽ ልቤ ተቃጠለ
የመለየት እሳት እያቃጠለኝ
ልቤ ተው እያለ በአፌ ሂጂ አልኩኝ
ሂጂ ብልሽ በአፌ አይደል ጠልቼሽ
ማጣት ነው ያሰረኝ እንዳላስቀርሽ
እንዳላስቀርሽ
ፍቅር ነው 2X
የኔ አለም ፍቅር ነው
ፍቅር ነው 2X
ያቃተኝ መለየቱ ነው 2X
ያቃተኝ ካንቺ መራቅ ነው
2X
ያቃተኝ መሸኘቱ ነው
ያቃተኝ ካንቺ መራቅ ነው
2X
ሸኘሁሽ ሳልወድ ጨክኜ
ሆዴ እንቢ ቢለኝም እንደቻለ ሆኜ
መሄድሽን ሳስበው ቢያመኝም
መልሶ ያመጣሻል አምላክ አይተወኝም
2X
ሰላም ሁን ብለሽኛል ምን ሳላም አገኝ ብለሽ
ሰው ፍቅሩን እራሱን አቶ ነግቶለት እንዴት ይመሽ
ከፍቶኛል አልልሽም ውስጥሽን ልረብሸው
በእንባዬ እየራስኩኝ ሰላም ነኝ ብዬ ዋሸው 2X
ይልቅ ባይጠቅምሽም አይሆንሽ ብርታት
መጸለይ ነው መልካም ይሁንሽ ጽናት
አደራ እለዋለው ወድቄ ከደጁ
አያሳፍረኝም ሁሉ ሞልቶ በጁ
ሰላም ያግሽና ሰላም ይመልስሽ
ያላንቺ ጨልሟል ያደመቅሽው ቤትሽ
ፍቅር ነው 2X
የኔ አለም ፍቅር ነው
ፍቅር ነው 2X
ያቃተኝ መለየቱ ነው
ያቃተኝ ካንቺ መራቅ ነው
2X
ያቃተኝ መሸኘቱ ነው
ያቃተኝ ካንቺ መራቅ ነው
2X

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO