LYRIC

ስሌት የማይፈታው
መልስ የማይመልሰው
የሌለው ማርከሻ
ስሙ ቢሆንብኝ
የቃላት የቅኝት የከንፈር ማማሻ
የዜማ የዜማ የሃሳቤ መነሻ መድረሻ
መነሻ መድረሻ 2X
አለሜ ነው ለኔ እሱማ ለኔ
እሱማ የትንፋሼ ዜማ
አውቀው ቢያሳውቁኝ ምናለ ለኔ
ምናለ ፍቅር የቱጋ እንዳለ
2X
አዬሄሄሄ ሆኖ አንዳንዴ የኮከብ መጋጠም
አዬሄሄሄ መልስም ጥያቄ ነው የስሜቶች መስጠም
አዬሄሄሄ ወይናደጋ አይሞቀው አይበርደው
አዬሄሄሄ አንደ ሀይ ሰንበሌጥ ልቤን ከራ
አዬሄሄሄ 3X
ጥሎብኝ እሱን ወድጃለው
ካልመጣስ እንዴት እሆናለው
ነግሶብኝ በኔ ከከረመ
ለምን ወደድሽው እንዳትሉኝ
ደርሶበት ያየ እስኪ ይፍረደኝ
ጥሎብኝ 4X
ቀልቤ ከተራጋ
ቀልቤ ከተረጋ የሱን ስም ተርታቹ
ሀሰት ነው መኖሬ
ውሸት ነው መኖሬ እኔው ልንገራቹ
የፍቅር ልክ ሆኖ
የመውደድ ጥግ ሆኖ በኔው ከራርሞብኝ
እንዴት ወደደችው
እንደምን ወደድሽው ባካችሁ አትበሉኝ
ጥሎብኝ እሱን ወድጃለው
ካልመጣስ እንዴት እሆናለው
ነግሶብኝ በኔ ከከረመ
ለምን ወደድሽው እንዳትሉኝ
ደርሶበት ያየ እስኪ ይፍረደኝ
ጥሎብኝ 4X
አዬሄሄሄ መልስ የምጠይቁኝ ምኑን ነው ብላቹ
አዬሄሄሄ ወደድኩት እሱን ብዬ ልንገራቹ
አዬሄሄሄ ቀስተ ደመና ህብር የበዛበት
አዬሄሄሄ እንዲያ የሚሆንባችሁ እንዲህ ነው ስትሉ
ምኑን ነው አይኑን ነው
ምኑን ነው ጥርሱን ነው
አልልም አንዴ ወድጃለው
ካልመጣስ እንዴት እሆናለው
ነግሶብኝ በኔ ከከረመ
ለምን ወደድሽው እንዳትሉኝ
ደርሶበት ያየ እስኪ ይፍረደኝ
ጥሎብኝ 12X

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO