LYRIC

ጠቀስ
ጠቀስ አርጊና
3X
አርጊና አርጊና
ይመቻል ምሽቱ
አንቺ ካለሽ እቱ
2X
አንቺዬ ገና እግርሽ ሲረግጥ
ሆድዬ ስትገቢ ከበሩ
አንቺዬ አይኔስ አወቀብኝ
ሆድዬ ልቤ መሸበሩን
አንችዬ ቃል ከአፌ ባይወጣ
ሆድዬ ቃላት ባልናገር
አንቺዬ አይኔ ይጠብቃል
የኔ አለም ከአይንሽ አንድ ነገር
ከንፈርሽ ሲላወስ ጥርስሽ ይስበኛል
ዜማ አለው ቅላጼን ጨዋታሽ ያምረኛል
ደሞ ደሞ ደሞን ስትወዛወዢ
አቤት ደሞ ደሞን አይን የምታፈዢ
ኧረ ደሞ ደሞን እንዳይገለኝ በፍቅር
ኧረ ደሞ ደሞን እንዳልደናበር
ኧረ ደሞ ደሞን ወደኔ ነይና
ልቤ ደስ ይበለው ጠቀስ አርጊኝና
ጠቀስ
ጠቀስ አርጊና
3X
እንበል ፈታ ዘና
2X
ጠቀስ
ጠቀስ አርጊና
3X
አርጊና አርጊና
ይመቻል ምሽቱ
አንቺ ካለሽ እቱ
2X
አንቺዬ የሰራ አካላትሽን
ሆድዬን ከምን ነው የሰራው
አንቺዬ ገና ከሩቅ ሲያዩሽ
የኔ አለም አይንሽ የሚያበራው
አንቺዬ በነጋ በጠባን
የኔ አለም ወደ አንቺ የሚወስደኝ
አንቺዬ አይንሽ አይደለም ወይ
የኔ አለም እኔን ያሳበደኝ
በመንገድ ላይ ያየኝ ይማርህ ይለኛል
እኔ ገና አልዳንኩም ጭራሽ ብሶብኛል
ደሞ ደሞ ደሞን አይኔም ያመኛል
ደሞ ደሞ ደሞን ልቤንም ያመኛል
ደሞ ደሞ ደሞን ሀኪም እንዳትወስዱኝ
ደሞ ደሞ ደሞን መርፌውን ፈራለው
ደሞ ደሞ ደሞን መድሀኒቴ እሷ ናት
ደሞ ደሞ ደሞን በጥቅሻዋ ድናለው
ጠቀስ
ጠቀስ አርጊና
3X
እንበል ፈታ ዘና
2X
ጠቀስ 6X

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO