LYRIC

ተማጸንኳት ጠናው ደጅ
ባስለምናት በአማላጅ
ይቅር በቃን እያለችኝ
አለሁ ብላ ተለየችኝ
ጉድ ሰራችኝ አዬ
ጉድ ሰራችኝ ዋይ ዋይ
ጉድ ሰራችኝ አዬ
2x
አንቺን እያለ እንጂ ያባከነኝ ነብሴ
አላንስም ነበረ እኔማ ለራሴ
ያጠፋ በጸጸት ልቡን ከመለሰው
ይቅር አይልም ወይ የተበደለ ሰው
እንዳረሳት ናፍቆቴን
እንዳልተዋት ጭንቀቴን 2x
ወትሮም ልቤም ጥፋቱ
አንቺ አለሽ የማለቱ 2x
ሆዴ ናፍቆ ቢነድ እንደ እሳት
አይችልም ሰው መርሳት
የልቤ እዳ ሆነሽ ጨነቀኝ
አንቺን እያሰኘኝ
2x
ተማጸንኳት ጠናው ደጅ
ባስለምናት በአማላጅ
ይቅር በቃን እያለችኝ
አለሁ ብላ ተለየችኝ
ጉድ ሰራችኝ አዬ
ጉድ ሰራችኝ ዋይ ዋይ
ጉድ ሰራችኝ አዬ
2x
በኩል እንዳልያዝነው ፍቅርን አቻ ላቻ
አንቺ የኔ ሆነሽ እኔም ያንቺ ብቻ
ኪዳናችን ሰምቶ ብዙ አይተን በፍቅር
አበባው ፍቅራችን ተቀጨ በጅምር
እንዳረሳሽ ናፍቆቴ
እንዳትረሽኝ ጭንቀቴ
እንዳልተውሽ ጭንቀቴ
ወትሮም ልቤም ጥፋቱ
አንቺ አለሽኝ የማለቱ 2x
ሆዴ ናፍቆ ቢነድ እንደ እሳት
አይችል ሰው መርሳት
የልቤ እዳ ሆነሽ ጨነቀኝ
አንቺን እያሰኘኝ
2x
ተማጸንኳት ጠናው ደጅ
ባስለምናት በአማላጅ
ይቅር በቃን እያለችኝ
አለሁ ብላ ተለየችኝ
ጉድ ሰራችኝ አዬ
ጉድ ሰራችኝ ዋይ ዋይ
ጉድ ሰራችኝ አዬ
2x

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO