LYRIC

ገና እንዳዩሽ(3) ውበትሽ ማርኳቸው
ገና እንዳዩሽ(3) ጭፈራሽ ለገዛቸው
እያንዳዱ ሁሉም የራሱ ውበት አለው
እያንዳንዱ በተፈጥሮ የታደለው
ምንም ያህል ቢታደሉ ውብ ቁመና
በመልካም ልብ ካልታጀበ የለው እርባና
አንድም ምሳሌ አንድም የሷ ፀባይ
ተችሯታል መባሏ ከላይ
ሁሉም ሚወደው ግሩም በህሪ
አላት እሷ አክብሮት ለፍጡረ ለፈጣሪ አንዱሁለተም የሷ
ውበት
ስቦ ያስቀራል ከመሬት ስበት
ፀዳል ነው ፊቷም ጨዋ ሰውነት
ሁሉም ሰው ይሰማማል በአንድ አንደበት
ዐይኗ እንደከዋክብት ያበራል
ልቧ ሁሌም ፍቅር ይዘራል
ፈገግታዋ ነው ሚሊየን
ለከፋውም ሁሉ መፅናኛ ሚሆን
ውበቷ ቢታይም ገኖ
ተፈጥሮም በላዩዋ ከብሮ
ሁሌም ናት እሷ መልካም
በውበቷ አትመካም
ገና እንዳዩሽ(3) ውበትሽ ማርኳቸው
ገና እንዳዩሽ(3) ጭፈራሽ ለገዛቸው
ወርሳለች ጨዋነትን ከእናቷ
ታታሪ ነች ብልህ አነደአባቷ
ለምዶ
ባህር ተሻግራ ማዶ
ብትሄድም ተጉዛ
ደርሳለች በያዘችው ጎዳና
ተቀምጣለች ይኸው ከውበት ማማ
ለምዶ
ባህር ተሻግራ ከማዶ
ይቺ ደፋር እዩዋት አንድ ጊዜ
በወንዶች ዐለም የሆነች ተምሳሌት
ይቺ ደፋር እዩዋት ካሉት በሙሉ
የሷ ተገን መሆን ሊሆኑ ሲጥሩ
ይቺ ደፋር እዩዋት አንድ ጊዜ የሴት ጀግና
ፅናቷ ያለው ለያዘችው አላማ
ይቺ ደፋር እዩዋተ አንበሳ ስትሆን
የምትጠብቅ የሴት ልጅ ወጉን ወጉን
ገና እንዳዩሽ(3) ውበትሽ ማርኳቸው
ገና እንዳዩሽ(3) ጭፈራሽ ለገዛቸው
እያንዳዱ ሁሉም የራሱ ውበት አለው
እያንዳንዱ በተፈጥሮ የታደለው
ምንም ያህል ቢታደሉ ውብ ቁመና
በመልካም ልብ ካልታጀበ የለው እርባና
አንድም ምሳሌ ሶስትም አራት አምስት የሰላምና የፍቅር
ንግስት
ትሰራለች ካለገደብ
ያለአድሎ ለሁሉም ወገን
የተለየች የሰው ፍጡር
ጥላቻ አታውቅ ያላት ፍቅር
እስኪ ሁላችንም አንዴ ክብር
እንስጣት በእንዲህ
ብሩህ ልጅ ነች እሷ ነች አስተዋይ
ስብዕናዋ ሳበኝ ከመልኳ በላይ
አትባክን ለባዶ ፍልስፍና
ለአምላኳም የላት ስንፍና
አይሰለችኝም ሁሌም ባነሳት
አበዛባትም የለነጂ ቢያንሳት
የምትሆን ነች ለስንቱ ምሳሌ
ከጎነሽ አልለይም ሁሌ

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO