LYRIC

ዛሬ ቀኔ ነው ከእሷጋር ነው የማድረው
(ዛሬ ቀኔ ነው ከእሷጋር ነው የማድረው)
ዛሬ ድሌ ነው ከእሷ ጋር ነው ማድረው
(ዛሬ ድሌ ነው ከእሷ ጋር ነው ማድረው)
ተብሎ አበባዬ ውሮ ወሸባዬ
(ተብሎ አበባዬ ውሮ ወሸባዬ)
2X
እምቢ ገለሌ…….ገለሌ 4X
የፍቅር እናት ቃሏን አክባሪ
ገለሌ
እንኳንስ መልኳ ስሟ ተጠሪ
ገለሌ
ሰፋ ሰፋ አርጉት መታለች ቆንጆ
ገለሌ
ከኔ ጋር ልትኖር ልትሰራ ጎጆ
ገለሌ
እምቢ ገለሌ…….ገለሌ 4X
እይዋት ዝምብላ ቃል ሳታወጣ
ገለሌ
ሲያወሩ ሴቶች ተሰማች በልጣ
ገለሌ
በይ ተሰናጂ ጓዝሽን ያዢ
ገለሌ
ጥበብ ሰንደቁን ሸማ ልበሺ
ገለሌ
ነው ልወስድሽ ላልመልስሽ
(ነው ልወስድሽ ላልመልስሽ)
ዘራፍ ልፎክር አጅበን ወገን
ገለሌ
ሚለየን የለም ፍቅሬና ሀገሬን
ገለሌ
ጀግና ነኝ በጣም እኔ ደሳለኝ
ገለሌ
ያለምን እሺ ላንቺ ከጣልኩኝ
ገለሌ
ነው ልወስድሽ ላልመልስሽ
(ነው ልወስድሽ ላልመልስሽ)
እልሌ ቻቻ እልሌ ድም ድም
(እልሌ ቻቻ እልሌ ድም ድም)
2X
ሆ በል ጎበዜ
እልሌ
ተነስ አሁን
ነገ በደስታ
እልሌ
ላንተ እመኛው
እልሌ
ሲያምረው ይቅራ
እልሌ
ሁሌ የሚመኘው
እልሌ
ባይኑ ቢሸኛት
እልሌ
እጇን አይ ይዞ
እልሌ
የዛተው ሁሉ
እልሌ
ወንድ ነው እንዴ
እልሌ
እስኪ ከመጣ
እልሌ
አይዝለም ክንዴ
እልሌ
ደከመኝ ተወኝ
እልሌ
ብሎ ከማለ
እልሌ
አይችልም ሆዴ
እልሌ
በማርያም ካለ
እልሌ
እልሌ ቻቻ እልሌ ድም ድም
(እልሌ ቻቻ እልሌ ድም ድም)
2X
ና ወገኔ ጠጋ በል ጠጋ
ቁጭ አትበል ጨፍር አትስጋ
ስትነሳ ያኔ ደስ አለኝ
ማነህ ጎበዝ ውጣ ግጠመኝ
ወሌ ወሌ 4X
እልሌ
ያየ ምን ይላል
አትሁን ሰነፍ
መቼ ቻልክና እኔን ማሸነፍ
ከደፋር ጎበዝ ገጥመሃል አሉ
በርታና ጨፍር
ይድመቅ በሃሉ
ወሌ ወሌ 4X
እልሌ
2X

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO