LYRIC

ይሰማል
ይሰማል ደውል
በቀኝ የሚያዋውል
ይሰማል ይሰማል ያው ደውል
ከፍ ካለው አምባ
አንጀት እያባባ
ስማው ልቤ ሲያስተጋባ
ሰው ከሰው ሲያግባባ
ይሰማኛል ቃል ከማዶ
ፈውርን ሲያዜም እርቅ አውርዶ
(ይሰማኛል ቃል ከማዶ
ፈውርን ሲያዜም እርቅ አውርዶ)
ይሰማኛል ከዚያ ጎራ
የተስፋው ድምጽ የሚጣራ
(ይሰማኛል ከዚያ ጎራ
የተስፋው ድምጽ የሚጣራ)
ስንት እየቻለ ባኖረኝ ሀገር
ብርቅ አይደለም ተው መከባበር
ዘዴው ሳይጠፋህ ችሎ ማለፉ
አታርገኝ ልቤ ያን ሰው ጤፉ
(ወይም አልተራብክ ወይ አልተጠማህ
ለምንስ ይሆን ድምጽ ያልተሰማህ)
እሺ ነው መልካም በጀ በል ሆዴ
መዋደዱ ነው ጥንትም ልምዴ
ጸንቶ ለመዝለቅ በፍቅር ቃሉ
አይበጅም ከሰው መነጣጠሉ
(ወይም አልተራብክ ወይ አልተጠማህ
ለምንስ ይሆን ድምጽ ያልተሰማህ)
እህ በልልኝ ደውሉን ስማ……..እህ
ደውሉን ስማ………እህ
በጀ በል ሆዴ ከሰው ታርቄ ከኔው ልስማማ
እሺ በል ልቤ ከሰው ታርቄ ከኔው ልስማማ
በጀ በል ሆዴ
(ከሰው ታርቄ)
እሺ በል ልቤ
(ከኔው ልስማማ)
በጀ በል ሆዴ
(ከሰው ታርቄ)
እንዲያ ነው ልምዴ
(ከኔው ልስማማ)
ይሰማኛል ቃል ከማዶ
ፈውርን ሲያዜም እርቅ አውርዶ
(ይሰማኛል ቃል ከማዶ
ፈውርን ሲያዜም እርቅ አውርዶ)
ይሰማኛል ከዚያ ጎራ
የተስፋው ድምጽ የሚጣራ
(ይሰማኛል ከዚያ ጎራ
የተስፋው ድምጽ የሚጣራ)
ከአበው ባደራ ቀን ያቆየሁት
ስንት አለኝ ገና ያላየሁት
ለመገላመጥ ካላታገለ
በቂ ነው አንገት ራስ ከቻለ
(በቸር ከታየ ኋላ እና ፊቱ
መች ያዳግታል ይቅር ማለቱ)
ባንደኛው ጸሎት ያንዱ መከራ
ሲያልፍ እያየኧው በየተራ
ታሪክ ላይጻፍ በቂም ተሻግሮ
ጸጸት ነው ትርፉ ተው አምባጓሮ
(በቸር ከታየ ኋላ እና ፊቱ
መች ያዳግታል ይቅር ማለቱ)
እህ በልልኝ ደውሉን ስማ……..እህ
ደውሉን ስማ………እህ
በጀ በል ሆዴ ከሰው ታርቄ ከኔው ልስማማ
እሺ በል ልቤ ከሰው ታርቄ ከኔው ልስማማ
በጀ በል ሆዴ
(ከሰው ታርቄ)
እሺ በል ልቤ
(ከኔው ልስማማ)
በጀ በል ሆዴ
(ከሰው ታርቄ)
እንዲያ ነው ልምዴ
(ከኔው ልስማማ)
2X

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO