LYRIC

የአዲስ ቀን ጸሀይ ጠዋት እንዲወጣ
ይጨላልማል ነገ እንዲመጣ
እንዳትፈራ ልቤ በእምነትህ ጽና
ሲያልፍ ይደራረባል ሁሌም ፈተና
አለሜዋ እንዳይከፋሽ እንዳይከፋሽ
በጭራሽ እንዳይከፋሽ እንዳይከፋሽ
ደርሰህ የረገጥካት መሬት
ወድቀህ ከጫፍ የምታያት
ትናንት የጋረደህ አድማስ ነው
ዛሬ የቆምክበት የተራራ አናት
እራት ወሬ አይወልድም አይሆንም መሸሸጊያ
ተስፋው ነው የታጋሽ መጠለያ
መሃሉም አይንካኝ በእምነት ተስፋ አድርጌ
እንባዬን በእጄ አብሼ
ቀና እያልኩኝ መልሼ
የደስታ እንጂ ከዚህ ወዲያ
የሀዘን የለኝም ህምባ ሆድ ብሼ
አለነገር መቼም አይሆን
አለነገር አላለም ዝም
አለ ስታይ እጅን በአፍ ላይ
እስኪያጭን ምክንያት የሚያስገርም
አየሁት ስቀርብ
አየሁት ስደርስ
የትናንት ማዘን
ሲገረሰስ
አየሁት ስደርስ
አየሁ ስጠጋ
የትናንት ማዘን
ዙሪያው ሲናጋ
እንዳትፈራ ልቤ በእምነትህ ጽና
ሲያልፍ ይደራረባል ሁሌም ፈተና
አለሜዋ እንዳይከፋሽ እንዳይከፋሽ
በጭራሽ እንዳይከፋሽ እንዳይከፋሽ
መሀል መንገድ የለም ምን እናርግ
ግማሽ ስሜት አይኖረኝ
ፍጻሜ አለው የኔም ተስፋ
ያሳየኝ ህመሜን አይነሳኝም
ሳያስፈራ የሚገርም
ሳያስቅ የሚደንቅ
አለ አዲስ ህይወት የተስፋ ስንቅ
የጀግና ልቡ ሩቅ ከእምነት ጋር ሲሆን ፍቅሩ
ሰላምን ይሰራል
ቢጻፍ ይጎላል ንዶ
ከለሊት አለው ንጋት
እንዳለ ሲፈታ ህልሙ እንኳን
እንኳን ሆነ ለዚ ነበር
የሚያስብል ፍጻሜ አለ
ያልታየ ያልተሰማ
አለኝ አዲስ ህይወት ለኔ የተባለ
ከፍቶሽ እንዳላይ በጭራሽ በጭራሽ
እንዳይከፋሽ እንዳይከፋሽ
አልይሽ ከፍቶሽ በጭራሽ በጭራሽ
እንዳይከፋሽ እንዳይከፋሽ
2X

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO