Warning: Creating default object from empty value in /home/ethiolyrics/public_html/wp-content/themes/muusico/framework/admin/ReduxCore/inc/class.redux_filesystem.php on line 29
የኔ – EthioLyrics – Ethiopian Lyrics & Video

LYRIC

የኔ 2X
እኔማ አንቺን አንቺን ብዬ
በናፍቆት አለንጋ
ባንቺው ተገርፌ
የኔው ነሽ ብዬ
ልቤን አስረክቤሽ
2X
ሁኝ ከልብሽ ፍቅሬን ከፍቅርሽ
ውስጤ የሚያልምሽ ሁሌ
የአይኔ ስስት የልቤ ንግስት
አንቹ ነሽ ለኔ ነይ
2X
የደስታዬ ፍሬ የሳቄ መክፈቻ
አድርጎ ፈጥሮሽ አንቺን ለኔ ብቻ
እርቄሽ እርቀሽ ብጠፊ ከአይኔ
ዛሬ ባገኛት ውልሽ አትራቂ ከጎኔ
ከፊትም ከኋላም ከግራም ከቀኝም
አንቺን በማለቴ ስንት ሰው ሲያማኝ
አልሰማህም በቃ አልሰማህም እኔ
ማንም አይምጣብኝ በሷ እና በአይኔ
ፍቅር ፍቅር ፍቅር ብሎ
ልቤ አንቺን አንቺን ብሎ
እኔን ጥሎ መቶልሻል
ውዴ የኔ የኔ ይልሻል
2X
እኔማ አንቺን አንቺን ብዬ
በናፍቆት አለንጋ
ባንቺው ተገርፌ
የኔው ነሽ ብዬ
ልቤን አስረክቤሽ
2X
ሁኝ ከልብሽ ፍቅሬን ከፍቅርሽ
ውስጤ የሚያልምሽ ሁሌ
የአይኔ ስስት የልቤ ንግስት
አንቹ ነሽ ለኔ ነይ
2X
ነይ ወደኔ ጥፊ
የፍቅሬ ዳርቻ በውበት ድንበር የሌለሽ አቻ
አላፊው አግዳሚው ቆሞ ያስተዋላት
ውበት ከቆንጅና አሟልቶ የሰጣት
ጸባይ ከመልክ ጋር ሁሉንም ያደላት
የውበት አድማቂ አይን ማረፊያ ናት
ከላይ የተላከች ለብቸኝነቴ
ሙሉ ላረገችኝ ውዷ እመቤቴ
ላመስግነው እኔ ላመስግነው በቃ
እሷን ለኔ ላረጋት ለሰማዩ ጌታ
ፍቅር ፍቅር ፍቅር ብሎ
ልቤ አንቺን አንቺን ብሎ
እኔን ጥሎ መቶልሻል
ውዴ የኔ የኔ ይልሻል
3X

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO