Warning: Creating default object from empty value in /home/ethiolyrics/public_html/wp-content/themes/muusico/framework/admin/ReduxCore/inc/class.redux_filesystem.php on line 29
የኔ ፍቅር – EthioLyrics – Ethiopian Lyrics & Video

LYRIC

ባትኖርም ካጠገቤ ከጎኔ ብትለየኝም
እኔስ አይሃለሁ አንተ ባታየኝም
ሳይህ ሳይህ ባድር ብዉል አይወጣልኝም
ፍቅር ያንተስ ፍቅር ፍቅር ያንተስ ፍቅር
ካጠገብህ ሁኘ ባላጫዉትህም
ገላህን አቅፌ ምንም ባልስምህም
በመንፈስ ካንተዉ ነኝ መቸም አልለይም
በሃሳብ መነጸር ሁሌ ነዉ የማይህ
ዉቅያኖስ ባህሩ አድማስ ብጋርደኝ
ወሳንተ መምጣቴን ማንም አያግደኝ
መምጫ መንገድ ሁሉ ቢዘጋ ቢታገድ
ፍቅር ያደርሰኛል ባሳብ አየር መንገድ
የኔ ፍቅር ፍቅር አገናኝተህ ከምትለየኝ
የኔ ፍቅር ፍቅር ምነዉ በፊት ባታሳየኝ
የኔ ፍቅር ፍቅር ወይ ዉሰደኝ ወይ አምጣልኝ
የኔ ፍቅር ፍቅር ያለዚያማ ጉዴ ነዉ እንጃልኝ
ቀኑን በትካዜ ብቻየን ሳወራ
ደግሞ ሊተካልኝ ሌሊቱም በተራ
ገና ገደም እንዳልኩ ካልጋዉ ስንገናኝ
የሃሳብ ሰመመን ጉዞ ነዉ የሚቀናኝ
ድንገት ከተፍ ስል ካለህበት ቦታ
እየተላቀስን በናፍቆት በደስታ
ታዲያ ምን ያደርጋለ ነበር ቢሆን በዉኔ
ለካስ በህልሜ ነዉ የማገኝህ እኔ
የኔ ፍቅር ፍቅር እዉን አርገዉ ፍታዉ ህልሜን
የኔ ፍቅር ፍቅር እንድወጣዉ ርሃብ ጥሜን
የኔ ፍቅር ፍቅር ወይ ዉሰደኝ ወይ አምጣልኝ
የኔ ፍቅር ፍቅር ያለዚያማ ጉዴ ነዉ እንጃልኝ

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO