LYRIC

ተምሬሽ በልቤ ጸሀይ አኑሬሽ በልቤ ሻማ
ነይ ስልሽ ነይ ነይ ነይልኝ የማታ የማታ ማታ
ሆነሽኝ የፍቅር ኪዳኔ ሀ ፊደል ጅማሪዬ
የልቤ ቀለም ቅቤ ነሽ ፍቅርን ያጣጣምኩብሽ
የኔታዬ ሀሁ ፊደሌ 3X
የፍቅሬ የልቤ ክታብ የሆንሽኝ አዱ ድርሳኔ
ልሳኔ ለኔ ለልቤ አንቺው ነሽ መድሀኒቴ
ሳይሽም የምረካው ስጠራሽ የምደሰተው
አርጌሽ የኔ የግሌ የልቤ ለጋሲ ቃሌ
የኔታዬ ሀሁ ፊደሌ 4X
ስትርቂኝ እኔ ሰጋለው ስትቀርቢኝ እደሰታለው
ፍቅርሽም እስትንፋሴ ነው የምኖረው በሱ ብቻ ነው
ላወድስሽ ብጥርም ብዙ ቃል ባንደራድርም
የሆዴን ልቻል ብዬ ጠራሁሽ ብዬ የኔታዬ
የኔታዬ ሀሁ ፊደሌ 4X
ተምሬሽ በልቤ ጸሀይ አኑሬሽ በልቤ ሻማ
ነይ ስልሽ ነይ ነይ ነይልኝ የማታ የማታ ማታ
ሆነሽኝ የፍቅር ኪዳኔ ሀ ፊደል ጅማሪዬ
የልቤ ቀለም ቅቤ ነሽ ፍቅርን ያጣጣምኩብሽ
የኔታዬ ሀሁ ፊደሌ 8X

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO