Warning: Creating default object from empty value in /home/ethiolyrics/public_html/wp-content/themes/muusico/framework/admin/ReduxCore/inc/class.redux_filesystem.php on line 29
የተለየሽ – EthioLyrics – Ethiopian Lyrics & Video

LYRIC

የማለዳዋ ጸሀይ የማታ ጀምበር
ቅኔ መፍቻ የሆንሽልኝ
ልዩ
ህይወት ሰጠኝ በትንሳሄ ፍቅርሽ ዳግም
በፍቅር ውዴን አግኝቻለው
ደስታን ሰጠኝ
እንደ ንጋት ወፍ ዝማሬ
ስትኖሪ ጎኔ ፍቅሬ
ውብ ይሆናል ቀኔ በርቶ
ፍቅርሽ ሀዘኔን ተክቶ
2X
እንደ ገዳም እጣን ጠረንሽ ከሩቅ ሁሌ እየጠራኝ
የውበትሽ ግርማ ልቤ ውስጥ ገብቶ ላንቺው ሲያኖረኝ
በክዋክብት ደምቆ እንደሚጣየው የጠራው ሰማይ
ፈገግታሽ ልዩ ነው ብርሀን ይሞላል ጨረቃን መሳይ
እንደልጅነቴ እንደምጠብቅ እንቁጣጣሽ
ሀሴት አገኛለው አይንሽን ላየው ስቆም ከፊትሽ
በክዋክብት ደምቆ እንደሚጣየው የጠራው ሰማይ
ፈገግታሽ ልዩ ነው ብርሀን ይሞላል ጨረቃን መሳይ
መለኪያዬ የልቤን ድምጽ ተጎናጸፍኩ ባንቺ እንደ አዲስ
እውነተኛ ፍቅር ዘማሪ ለኔ እኮ ነው አንቺ የምትኖሪው
2X
የማለዳዋ ጸሀይ የማታ ጀምበር
ቅኔ መፍቻ የሆንሽልኝ
ልዩ
ህይወት ሰጠኝ በትንሳሄ ፍቅርሽ ዳግም
በፍቅር ውዴን አግኝቻለው
ደስታን ሰጠኝ
የበረሀ የዛፍ ጽድ
በፈገግታሽ ጥምን ቆራጭ
በአንድ እይታ ፍቅርን ዘሪ
እርግቤ ነሽ ደስታን ሰጭ
የፍቅር አዝመራ አረም የሌለው የመውደድ እሸት
በአይኖችሽ ይታያል የማይጠገበው የእናት ማንነት
ምን ይሆን ሚስጥሩ ባክሽ ንገሪኝ
ቅኔው ይዘለፍ
እያደር እንደወይን መልካምነትሽ ሁሌ የሚጣፍጥ
2X
መለኪያዬ የልቤን ድምጽ ተጎናጸፍኩ ባንቺ እንደ አዲስ
እውነተኛ ፍቅር ዘማሪ ለኔ እኮ ነው አንቺ የምትኖሪው
2X
እንደ ንጋት ወፍ ዝማሬ
ስትኖሪ ጎኔ ፍቅሬ
ውብ ይሆናል ቀኔ በርቶ
ፍቅርሽ ሀዘንን ተክቶ
3X

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO