LYRIC

አለም አየው ውበትሽን
ስንቱ ተመኘው ቆንጅናሽን
ኧረ እኔ አላየው አንቺን መሳይ
ያልጎደለሽ ከነ ጸባይ
2X
ውብ አለሜ ውብ አለሜ
ለኔ ለኔ ጣፋጭ ህልሜ
ቢያዩሽ ቢያዩሽ ቢዳስሱሽ
የለም አሉ ቢፈልጉ
2X
አየው በብሌኔ
ሲገጣጠም ጎኔ
ሲያበጅሽ ፈጣ ከኔ ወስዶ ለኔ
ምንኛ ታደልኩኝ አንቺን በማግኘቴ
ቆንጆ ጸባየ ሰናይ ስትገባልኝ ቤቴ
አሁን ገና በራልኝ አይኔ
አሁን ገና ሰመረልኝ ህልሜ
አልሰለችሽ ባይሽ ደጋግሜ
ተዋህዷል ደምሽ እና ደሜ
2X
አለም አየው ውበትሽን
ስንቱ ተመኘው ቆንጅናሽን
ኧረ እኔ አላየው አንቺን መሳይ
ያልጎደለሽ ከነ ጸባይ
2X
ውብ አለሜ ውብ አለሜ
ለኔ ለኔ ጣፋጭ ህልሜ
ቢያዩሽ ቢያዩሽ ቢዳስሱሽ
የለም አሉ ቢፈልጉ
2X
የተቸረችኝ ከላይ ያገኘሁሽ
የምኮራብሽ ነሽ አይኔን የማይብሽ
ምነኛ ታደልኩኝ አንቺን በማግኘቴ
ቆንጆ ጸባየ ሰናይ ስትገባልኝ ቤቴ
አሁን ገና በራልኝ አይኔ
አሁን ገና ሰመረልኝ ህልሜ
አልሰለችሽ ባይሽ ደጋግሜ
ተዋህዷል ደምሽ እና ደሜ
3X

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO