LYRIC

ቆንጅና ምንድነው
ሰዎች ንገሩኝ
እኔ እሷን በማየት ተብረከረኩኝ
ውበት ከሷ ጋራ
ነው የተፈጠረው
ቃላቶች ያጥሩኛል
እኔ ባላወራው
ውበትና……ቆንጅናሽ
ይማርካል ለሚያይሽ
2X
ቁመናሽ ግሩም ነው
እንከን አይወጣለት
አቤት ያለው ደስታ
አንቺን ያገኙ ለት
ያንቺን ውበት ማውራት
እንዲያው ለከንቱ ነው
ፈራጅ አስቀምጦ ፍጥረት ማስመስከር ነው
ውበትና…..ቆንጅናሽ
ይማርካል ለሚያይሽ
2X
አለም ያደነቀው አፈጣጠርሽ
ጸጉርና ትከሻሽ ሽንጥ ና ዳሌሽ
ብርቱካን ጉንጮችሽ ማራኪው ጥርስሽ
ኮከብ መሳይ አይንሽ ትርንጎ ጡትሽ
ውበትና…….ቆንጅናሽ
ይማርካል ለሚያይሽ
2X
ይማርካል ለሚያይሽ 3X

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO