LYRIC

እንደው ሙሉ ሆኜ ተፈጥሬ
በነገ ተስፋ ታጥሬ
ያጣሁ የሌለኝ ደርሶ ቢመስለኝ
ታውቄ
አወይ እግሬ……
ወስዶ አወጣኝ ከሀገሬ
2X
ንጹህ ፍቅር እምነት ሰላም ሳይጠፋ
ነገን የሚያኖር ተስፋ
ሁሉም ሞልቶ ሳለ
ከሀገር መንደሬ ስስት ከማታውቅ ምድሬ
ልቤ እሩቅ ተመኘ
ተሰማው ተረቶ ንቆ የራሱን ትቶ
ያሉት ከንቱ ቢያየው ቀርቦ ቢረዳ
ሆነበት የህሊና እዳ
ሁሁ
ወደ እናቴ ቤት እመለሳለው
ከውብ እቅፏ ልኑር ብያለው
3X
እንደው ሙሉ ሆኜ ተፈጥሬ
በነገ ተስፋ ታጥሬ
ያጣሁ የሌለኝ ደርሶ ቢመስለኝ
አወይ እግሬ……2X
ወስዶ አወጣኝ ከሀገሬ

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO