LYRIC

የልቤ ውብ ስጦታ

ታማኝ ሰው በዝምታ

ቀን ከሌት ሳስስ ኖሬ

ተገኘች ዛሬ

ስገረም በውበቷ

ቃል አጣሁ ላንደበቷ

አታምንም አቅርበሃት

ካላየሀት

ንቃ ንቃ ባል ተነሳ

ከዚህ በፊት ያለፈውን አትርሳ

ተጫዋች ነች

በቀሚሷ

እኔ አውቃታለው ብዙ አታውራ ስለሷ

አዝማች

ሀ……ሀ……ጨዋ አይደለችም

ሀ……ሀ……እሷ አይደለችም

ሀ……ሀ……ጨዋ አይደለችም

ዛሬ ካንተ ጋር ነገ ደግሞ ከሌላ ነች

ፍቅር ሳይሆን እሷ ገንዘብ በጣም ትወዳለች

ፎንቃ አስይዛ ወንዱን ሁሉ አሳብዳለች

ጨዋ መስላ እንጂ እሷ ከባድ አታላይ ነች

ነው……ለክብሯ አንገት ደፍታ

በፍቅር የምትረታ

በፍጹም ቃል ተወዳጅ

ናት ጨዋ ልጅ

ተቀምጣ በኔ ቦታ

ሳታውቃት ባሉባልታ

ኧረ ተው አትሳሳት

አታርክሳት

ኦ…….ወሬ ወሬ ወሬ ወሬ ብቻ

ወሬ ወሬ አሁንስ ሰለቸኝ

የሷ ምኗም አልተመቸኝ

አ…..አሸንግለኝ አውቃታለው እራሷ ነች

ስንቱን በሙድ ስባ ቀርባ ጨርቁን አስጥላለች

አዝማች

ሀ……ሀ……ጨዋ አይደለችም

ሀ……ሀ……እሷ አይደለችም

ሀ……ሀ……ጨዋ አይደለችም

 

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO