Warning: Creating default object from empty value in /home/ethiolyrics/public_html/wp-content/themes/muusico/framework/admin/ReduxCore/inc/class.redux_filesystem.php on line 29
ካሽው – EthioLyrics – Ethiopian Lyrics & Video

LYRIC

ሲያድል ለካ እንዲ ነው ሲሰጥ ፈጥሮሻል አርጎ ውበት
እመኚኝ በኔ ሞት እንዳንቺ የለም ያፈቀርኩት
ሲያድል ለካ እንዲ ነው ሲሰጥ ፈጥሮሻል አርጎ ውበት
እመኚኝ የኔ አለም እንዳንቺ የለም የወደድኩት የለም
ገላዬ እየራበው ሆዴ ጾሙን እያደረ 2X
ከቀልቤ የገባ ለኔ ማንም አልነበረም
ብቻዬን ያለሰው ጉዴስ ስገፋው ቀኑን 2X
ነፍሴን የምትሞላ ሙሉ ሴት አገኘው አንቺን
ይቅርብኝ እያልኩኝ ውቢት ማንንም ሳልነካ 2X
አቤት የመኖሬ መልካም ለበጎ ነው ለካ
ታግሼ መኖሬ መልካም ለበጎ ነው ለካ
ሳስስሽ ስፈልግሽ ስመኝሽ ከርሜ
እንኳንም መና አልቀረው ተሳካልኝ ህልሜ
አባዝነሽ አባዝነሽ ደጅ እያስጠናሽኝ
ያንገላታሽውን እስኪ ልቤን ካሺው
ካሽው በይ ልቤን ካሽው
ካሽው መውደድ ለግሽው
ካሽው በይ ልቤን ካሽው
አይዞህ እያልሽው
2X
ሲያድል ለካ እንዲ ነው ሲሰጥ ፈጥሮሻል አርጎ ውበት
እመኚኝ በኔ ሞት እንዳንቺ የለም ያፈቀርኩት
ሲያድል ለካ እንዲ ነው ሲሰጥ ፈጥሮሻል አርጎ ውበት
እመኚኝ የኔ አለም እንዳንቺ የለም የወደድኩት የለም
ምን ያደርጋል ገንዘብ ውቢት ምን ያደርጋል ወርቅ 2X
የታይታ ብልጭልጭ አለሜ የአንገት በላይ ሳቅ
ከሁሉም በላይ ነው ውቢት ውበት እና ጸባይ 2X
ፈጣሪ የሰጠሽ አሟልቶ የተቸረሽ ከላይ
ወድጄ አልጠላሽም ውቢት እስከዘላለሜ 2X
የመንፈስ የብርታት አካሌ ስጋዬ ነሽ ደሜ 2X
ባልበላም ባልጠጣም ግድ የለኝም እኔ
አጫውቺኝ ውብ አለም አትራቂኝ ከአይኔ
የትም ልሂድ አትበይ ቀልቤን አትረብሺው
ፍቅርን እየካደምሽ ይልቅ ልቤን ካሽው
ካሽው በይ ልቤን ካሽው
ካሽው መውደድ ለግሽው
ካሽው በይ ልቤን ካሽው
ጭንቁን አስረሽው
አይዞህ እያልሽው
2X

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO