LYRIC

ከቃል በላይ ሆኖብኛል ፍቅርሽ 2X
እኔስ ማን ልበልሽ
በምን ቃል ልግለጽሽ
2X
መላ ጨዋታሽ ቀልብን ይሰርቃል
ብወድሽ ያንስሻል
ከቶ አይጠገብም ሁሌም ይናፈቃል
ብወድሽ ያንስሻል
ለኔ ያለሽን ፍቅር ሳስበው ሁሌም
ብወድሽ ያንስሻል
አንቺን ማወደስ ሆኗል አመሌ
ብወድሽ ያንስሻል
እስኪ ተጫወች በይ ዘና
ደስታሽ ደስታዬ ነውና
ሁሌም ሳቅሽ ነው ምኞቴ
አዝነሽ አልይሽ በህይወቴ
ህይወቴማ ባንቺ ተገልጣለች
ታማኝ ፍቅር አዋቂ አግኝታለች
በቃሉ የሚታመን እውነተኛ
አድሎኛል ወዳጅ ነኝ ደስተኛ
ከቃል በላይ ሆኖበታል ፍቅርሽ
እሱ ቆይ አንቺን ማን ይበልሽ
ሲያማክረኝ የሚልሽ ቃል አቶ
እንዲጠራሽ አንድ ስያሜ ሰጥቶ
አልኩት ጠዋት ስትነሳ በላት የኔ አበባ
የፍቅር ቃል በውስጧ ላይ ዘልቆ እንዲገባ
አንቺማ
ጆሳንጋን መርተሻል ስንቱ ቢመላለስ
መች ያሳስትሻል
እሱን ካላሳሳትሽ ሳቅ አስቀድመሻል
ቆንጆ ብትረጂው እሱ ይሻልሻል
ከቃል በላይ ሆኖብኛል ፍቅርሽ 2X
እኔስ ማን ልበልሽ
በምን ቃል ልግለጽሽ
2X
ብርታቴ እኮ ነሽ ቀና ያልኩብሽ
ብወድሽ ያንስሻል
ውሎ እያደረቅሽኝ ደሞ እያማርኩብሽ
ብወድሽ ያንስሻል
መተኪያ የሌለሽ የፍቅር እናት
ብወድሽ ያንስሻል
አመሰግናለው አምላኬን በእውነት
ብወድሽ ያንስሻል
እስኪ ተጫወች በይ ዘና
ደስታሽ ደስታዬ ነውና
ሁሌም ሳቅሽ ነው ምኞቴ
አዝነሽ አልይሽ በህይወቴ
ህይወቴማ ባንቺ ተፈታለች
ታማኝ ፍቅር አዋቂ አግኝታለች
በቃሉ የሚታመን እውነተኛ
አድሎኛል ወዳጅ ነኝ ደስተኛ
2X

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO