LYRIC

አላስተባብርም አልበደልኩም ብዬ
ምክንያት አላመጣም እውነትን ከልዬ
የሆነውን ሁሉ በሚገባ አምናለው
ስላሳዘንኳቹ ይቅርታ አጥፍቻለው
ክርክሬ አለኝ የምለው እውነት
በዚህ ቆሜ የምነጋገርበት
እንድትሰሙኝ አጥብቄ የምፈልገው
እኔ የምለውን ነው
ስህተተኛ አይደለሁም 3X
አይደለሁም
እዛ አልቀረሁም
ንጹህ ሰው ነኝ ብዬ
አልደፍርም ልሞግት
ንጹህ አላማም እኔ
ጥቂት ነው የምታውቁት
ክርክሬ አለኝ የምለው እውነት
በዚህ ቆሜ የምነጋገርበት
እንድትሰሙኝ አጥብቄ የምፈልገው
እኔ የምለውን ነው
ስህተተኛ አይደለሁም 3X
አይደለሁም
እዛ አልቀረሁም
ስህተተኛ አይደለሁም 3X
አይደለሁም
እዛ አልቀረሁም
2X
የንጹህ ሀዘን እምባዬ
ይቅርታን አስተምሮኛል
ቅርርብንም ከአንድ አምላኬ
ከእንግዲህ ይበቃል ማፈሬ
አልቀርም መሮጤ ቀድሜ
ቀና ብዬም እራመዳለው
እንደማልደግመው ኖራለው
ስህተተኛ አይደለሁም 3X
አይደለሁም
እዛ አልቀረሁም
2X

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO