LYRIC

እንዴት አርጎሻል
አንቺስ ናፍቆቱ
አይታይሽም ወይ
አብሮ መብላቱ
ጤንነት አጣሁ
ደስታ እንደጥንቱ
ጎዳኝ ጭንቀቱ
ካንቺ ጋር ብኖር
እኔን ደስ ይለኛል
መለየት ለኔ
አንገላቶኛል
ሳላይሽ ውዬ ሳውቅ
በጣም ከፍቶኛል
ሳቅሽ ናፍቆኛል
ሁሌ አስብሻለው
በህልሜ ትመጫለሽ
በየደቂቃው ትዝ ትይኛለሽ
መለየት ክፉ እድል
መሀላችን ገብቷል
በእምባችን ብቻ ጠግቦ ማደር ይቅር
ምንም ቢመጣ እንጋፈጠው
ሞት አይምጣ እንጂ
ይገናኛል ሰው
ፍቅርዬ በርቺ ተዕግስት ይኑረን
እሱ ያለ ቀን እንገናኛለን
አንቺስ በቦታሽ ምን ተሰምቶሻል
ለኔ ያለሽ ፍቅር እንዴት አርጎሻል
እንዴት አርጎሻል
አንቺስ ናፍቆቱ
አይታይሽም ወይ
አብሮ መብላቱ
ጤንነት አጣሁ
ደስታ እንደጥንቱ
ጎዳኝ ጭንቀቱ
ካንቺ ጋር ብኖር
እኔን ደስ ይለኛል
መለየት ለኔ
አንገላቶኛል
ሳላይሽ ውዬ ሳውቅ
በጣም ከፍቶኛል
ሳቅሽ ናፍቆኛል
ሀሳብ ሲበረታ
ሲታይሽ የድሮው
አይክፋሽ ፍቅርዬ
አይክበድሽ ኑሮ
ጠንከር እንበልና
በተስፋ እንኑር
ምንም ቢያለያየን
የሩቅ ለሩቅ ፍቅር
ምንም ቢመጣ
እንጋፈጠው
ሞት አይምጣ እንጂ
ይገናኛል ሰው
ፍቅርዬ በርቺ ተዕግስት ይኑረን
እሱ ያለ ቀን እንገናኛለን
እምባዬ ሲፈስ
አንቺን በማጣት
እሱን እለዋለው
ካጠገቤ አትራቅ
አንቺስ በቦታሽ ምን ተሰምቶሻል
ለኔ ያለሽ ፍቅር እንዴት አርጎሻል
2X

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO