Warning: Creating default object from empty value in /home/ethiolyrics/public_html/wp-content/themes/muusico/framework/admin/ReduxCore/inc/class.redux_filesystem.php on line 29
እንዳይመሽ – EthioLyrics – Ethiopian Lyrics & Video

LYRIC

ገሃድ ሆኜ
ቤቱን ውጦታል ቅዠቴ
ናፍቆት ብሷል አንድም ከእናቴ አንድም ከቤቴ
ከአድማስ ባዶ ያለሽው ጎጆዬ እንዴት ነሽ
አይንሽ ናፍቆኝ ሳላይሽ ብቻ እንዳይመሽ
ጋራሽ ተራራው ሸንተረር ቁልቁለቱ
እንኳን ለአመታት ለአንድም ቀን መናፈቁ
ከመጪው ሂያጁ ስላንቺ መስማት ስራዬ
ዘንድሮ እንጃልኝ ጸሎትሽ ይርዳኝ እምዬ
በእንኮኮ ጉዞ በሀሳብ መንገድ
ሳልም የምኖር በናፍቆት ሆነብኝ
ሆድ ሁሉን እንዲችል ብሎ ቢል ተረቱ
ለሀገር ለእናት ሺው ለካስ ከንቱ ከንቱ
ሲመሽ ተመስገን ነው ማለቴ
የጥንት ውርሴ ነው ያውም ከእናቴ
እምዬ እናቴ ልቤ ደጊቷ
ደጇ ቢያደርሰኝ ይሄ ጸሎቷ 2X
ደጇ ቢያደርሰኝ አዛኝነቷ
የሾላ ዛፉ የአባ መምሬ
ብዙ የሚናፈቅ አለኝ ከሀገሬ
በእንኮኮ ጉዞ በሀሳብ መንገድ
ሳልም የምኖር በናፍቆት ሆነብኝ
ሆድ ሁሉን እንዲችል ብሎ ቢል ተረቱ
ለሀገር ለእናት ሺው ለካስ ከንቱ

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO