LYRIC

ተይ በልባችን ሁሉን ነገር አምቀን
ተይ ውሎ ሲያድር አንድ ቀን
ተይ ብንጣላ የለም የሚያስታርቀን
ተይ እንዳንቀር ተራርቀን
2X
ኩራት ክብሬ ስንል ነጋ ጠባ
እንደተኮራረፍን ሳንግባባ
ይቅርታ መጠየቅ መስሎን ሽንፈት
አልህ ባንጋባስ ምን አለበት
ውስጣችን እውነቱን እያወቀው
ለይምሰል በአፋችን ብንደብቀው
አንድ ቀን ተጣልተን ብንቀር መና
የሚለን ሰው የለም አባከና
ፍቅርና መቻቻል ባለበት
ፈጣሪም ይሰጣል በረከት
በህልህ ያለውን አፍርሰን
መገንባት ይከብዳል መልሰን
ተይ ተይ ተይ
ረጋ ብለሽ አስቢ ተይ
ይቅር ይቅር ይቅር
ሰላም ይኑረን ተይ
ተይ በልባችን ሁሉን ነገር አምቀን
ተይ ውሎ ሲያድር አንድ ቀን
ተይ ብንጣላ የለም የሚያስታርቀን
ተይ እንዳንቀር ተራርቀን
2X
አማላጅ ለጊዜው ቢያስታርቅም
እስከመጨረሻው አብሮ አይዘልቅም
ተይ ሚስጥራችንን አሳልፈን
ትዝብትና ጸጸት እንዳይተርፈን
ወይ አልተለያየን ቁርጡን አውቀን
ወይ አልተገናኘን ታርቀን
በአንድ ቤት እያለን ከአንገት በላይ
ምነው እንደደባል ባንተያይ
ከኔም ካንቺም ቢሆን ጥፋቱ
እያደር ይጠራል እውነቱ
ጥላቻን በፍቅር ሰርዘን
ብንኖር ይሻላል ታግሰን
ተይ ተይ ተይ
ረጋ ብለሽ አስቢ ተይ
ይቅር ይቅር ይቅር
ሰላም ይኑረን ተይ
2X

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO