LYRIC

እንቺ ከልብ ለወደዱት እንቺ ይሰጣል ልብማ
እንቺ ተንከባክበሽ ያዥው እንቺ በቀን በጨለማ
2X
በውበት መአዛሽ ነይ ገላዬ
ስፍስፍ ይላል ሆዴ ነይ ገላዬ
ተውበሽ ተውበሽ ነይ ገላዬ
ውዴ ፍቅሬ አይበቃሽም ወይ
ቀን በጸሀይ አይተዋትም በጨረቃም አይረሳትም
አንደበቴም ይጠየቃ አምኖባታል ልቤ በቃ
የኔ ነች የኔ ነች የኔ ብቻ
የሷ ነኝ የሷነኝ የሷ ብቻ
2X
ልክ እንደኔ ስለሷ መናገር እችላለው
ስሜቷን አውቀዋለው ወዳታለው
በመውደድ ብትረታኝ ከአንጀቴ ገብታ ውላ
የምሆንላት ጠፋኝ ለዚች ወለላ
ወለላ ነች ወለላ 3X
አንጀት የምትበላ ወለላ
2X
እንቺ ከልብ ለወደዱት እንቺ ይሰጣል ልብማ
እንቺ ተንከባክበሽ ያዥው እንቺ በቀን በጨለማ
2X
ሽቅብ ቁልቁል ልበል ነይ ገላዬ
አይደክምም ጉልበቴ ነይ ገላዬ
ትዝታሽ ስንቄ ነው ነይ ገላዬ
ውድ ፍቅሬ ሆንሽ መድሀኒቴ
ስጋ ፈራሽ ነፍስ ሀላፊ
ፍቅር ብቻ ነው ተራፊ
ይደር ካንቺ ከእንቁ ወርቋ
ይኧው ልቤን እንቺ በቃ
የኔ ነች የኔ ነች የኔ ብቻ
የሷ ነኝ የሷነኝ የሷ ብቻ
2X
ልክ እንደኔ ስለሷ መናገር እችላለው
ስሜቷን አውቀዋለው ወዳታለው
በመውደድ ብትረታኝ ከአንጀቴ ገብታ ውላ
የምሆንላት ጠፋኝ ለዚች ወለላ
ወለላ ነች ወለላ 3X
አንጀት የምትበላ ወለላ
4X

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO