Warning: Creating default object from empty value in /home/ethiolyrics/public_html/wp-content/themes/muusico/framework/admin/ReduxCore/inc/class.redux_filesystem.php on line 29
እቴ አባይ – EthioLyrics – Ethiopian Lyrics & Video

LYRIC

እኔ ያንተው ሰምና ወርቅ
ያንተው ቅኝ ያንተው ደሀ
እህ በለኝ አንተ ልጅ ወዝ
መስታወቴ በላ ልበልሀ
ሀ ግዕዝ ለ ግዕዝ በፍቅር ገበታ
አስተምረውናል ኮትኩተው የኔታ
ሀ ብለን ሳንቀንስ ለፍቅር ዘር ቆዳ
ስምክስ አለችኝ መልኬም ጠፋትና 2X
እቴ አባይ እቴ አባይ
እያልኳት እቴ አባይ
ገረመኝ ማተቧን ሳጣው አንገቷ ላይ
እቴ አባይ እቴ አባይ
እያልኳት ጢስ አባይ
ምን አሳስቧት ይሆን ዞረና እንለያይ
በፏፏቴው ብናኝ በረጠበው ፊቴ አይኗ ሳይላወስ
አድገን የለም ወይ ደስታውን ተላብሰን ከንፈር ስንቃመስ
ታዲያ ምነው አሁን ያችን ቀን በሀሳብ ታይቶኝ መርበትበቷ
ሳቅፋት የናፍቆቴን በማላውቅበት አፍ ማን ልበል ማለቷ
እጅ ሰቶ ለሞት ዘላለም ጥላ አካል ሳይቀደም
አፍ የፈቱበት ቃል የልጅነት ፍቅር ይወጣል ከደም
ያዋደደን ቀንቦ ፊደል ባህሩ ቢናድ ቢደፈርስ
ይከበራል እንጂ እንደምን ይረሳል መልዕክተ ዩሀንስ
እቴ አባይ እቴ አባይ
እያልኳት እቴ አባይ
ገረመኝ ማተቧን ሳጣው አንገቷ ላይ
እቴ አባይ እቴ አባይ
እያልኳት ጢስ አባይ
ምን አሳስቧት ይሆን ዞረና እንለያይ
መራራቅ እንጂ የገዳም አጥሩ
ለኔም ለሷም ነበር ቆም የመጫን ክብሩ
ወይ በኮሶ አትሽር ብዋትት አቶጣ
አብሰለሰለችኝ ከሆዴ ተቀምጣ
ከሆዴ ተቀምጣ
እቴ አባይ እቴ አባይ
እያልኳት እቴ አባይ
ገረመኝ ማተቧን ሳጣው አንገቷ ላይ
እቴ አባይ እቴ አባይ
እያልኳት ጢስ አባይ
ምን አሳስቧት ይሆን ዞረና እንለያይ
እንደ አጥቢያችን ደብር የመለከት አምባር አክሊለ ጉልላት
አልፎ ይገባ ነበር የአንገት ጥቤዋ ጌጥ የእጇላይ ንቅሳት
ቀን በቀን ሲገልጸው ከፍቅር ዳዊት ስሟን ስደጋግም
እንግዳው አመሏ ቆሻሸ መልክ በአይኗ ሳላገግም
ይብላኝ እንጂ ለሷ ላልዞረው መቀነት በውበት በአካሏ
ተምሮ ከፍቅር ከትናንቱ ዛሬ ላልከበረው ቃሏ
እኔማ በወረት ሰው አፍ እንዳንገባ ሆነና ጸሎቴ
እንደው ቢከፋኝ ነው አንተ ወራጅ ውሀ ተው ስማኝ ማለቴ
እቴ አባይ እቴ አባይ
እያልኳት እቴ አባይ
ገረመኝ ማተቧን ሳጣው አንገቷ ላይ
እቴ አባይ እቴ አባይ
እያልኳት ጢስ አባይ
ምን አሳስቧት ይሆን ዞረና እንለያይ
ወቅቱ በትዝታ ፍቅር ቢማርከኝ
እሷን እየበላት እኔን አሳከከኝ
ጠውልጎ ከስሩ ሳይጠፋ ቄጠማው
ይባላል ወይ ውሀ የአባይን ልጅ ጠማው
የአባይን ልጅ ጠማው 2X
እቴ አባይ እቴ አባይ
እያልኳት እቴ አባይ
ገረመኝ ማተቧን ሳጣው አንገቷ ላይ
እቴ አባይ እቴ አባይ
እያልኳት ጢስ አባይ
ምን አሳስቧት ይሆን ዞረና እንለያይ

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO