LYRIC

እስረኛሽን ፍቺው
እስረኛ
እስረኛሽን ፍቺው
ተይ አታንገላቺው
2X
ህግ ያሰረው እንኳን በጊዜው ይፈታል
ካህን ያሰረውም ካህን ይፈታዋል
ችሎቱ ተዛብቷል አሁን ድረስ ታስሯል
ያንቺኑ እስረኛ ማን ሰው ይዳኘዋል
ጭምት የሆነውን ልብሽን ክፈችው
ጽድቅ እንድታገኚ እስረኛሽን ፍቺው
በማይሆን አለም ውስጥ መኖርን እያሰብኩ
እኔነቴ ቀርቶ አንቺን እያሰብኩ
እስረኛሽን ፍቺው
እስረኛ
እስረኛሽን ፍቺው
ተይ አታንገላቺው
2X
መጻውቱን አይተሸ ከለሩን ንገሪኝ
ክዋክብቱን ቆጥረሽ ትዕዛዝ አሳውቂኝ
የልቤን ዳርቻ ግዝፈቱን ንገሪኝ
ፍቅርህ ምን ያህል ነው ብለሽ አጠይቂኝ
ጭምት የሆነውን ልብሽን ክፈችው
ጽድቅ እንድታገኚ እስረኛሽን ፍቺው
የተጣላ እንኳን በሸንጎ ይታረቃል
የእኔ እና ያንቺ ፍቅር ዳኛው ውሎት አድሯል

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO