LYRIC

ውዴ ፍቅርሽ ከልቤ ከአአንጀቴ
ዘልቆ ገብቶ በመላ አካቴ
እንዴት ብዬ መራቅሽን ልቋቋም
ብርታት ጽናቴም ከአንቺ ጋር እርቋል
2X
እርቀሺኝ አታውቂም በዚ ውሳኔ
እኔ ነኝ አዲስ
ምን ይሆን ምክንያትሽ ሆኖ ያገኘሽው
ከዚህ የሚያደርስ
ተዋደን ተላምደን ብዙ ተጉዘን
በፍቅር ጎዳና
ዛሬ ብትለዪኝ ጭንቀቴ በዛ
ናፍቆቴም ጸና
ፍቅሬ የታለሽ 2X
ጸናብኝ ናፍቆትሽ
ቀልቤ በምናብ ይመታል ሊያይሽ
ሊያሸፍተው ፍቅርሽ
ቀኑን እውልና ሳስብ
ለሊቱን አነጋለው ሳስብሽ
የትዝታሽ ድሩ ሸፍኖኝ
እንደ ልብ መላወስ አቃተኝ
ፍቅርሽ
አሸፍቶኝ ፍቅርሽ
8X
ውዴ ፍቅርሽ ከልቤ ከአአንጀቴ
ዘልቆ ገብቶ በመላ አካቴ
እንዴት ብዬ መራቅሽን ልቋቋም
ብርታት ጽናቴም ከአንቺ ጋር እርቋል
2X
አጥፍቼም ከሆነ ይቅርታ አርጊልኝ
ሁሉንም ተይው
ያለፈውም አልፏል ፍቅራችን ይንገስ
ነይ እናስምረው
እርቀሺኝ አታውቂም በዚ ውሳኔ
እኔ ነኝ አዲስ
ምን ይሆን ምክንያትሽ ሆኖ ያገኘሽው
ከዚህ የሚያደርስ
ፍቅሬ የታለሽ 2X
ጸናብኝ ናፍቆትሽ
ቀልቤ በምናብ ይመታል ሊያይሽ
ቢያሸፍተው ፍቅርሽ
የመለየት እጣን ታድዬ
መርሳትን አልቻልኩም ታግዬ
ተመለሺ ዋዪ ከጎኔ
ታደጊኝ ከጭንቀት ከሀሳቤ
ፍቅርሽ
አሸፍቶኝ ፍቅርሽ
8X

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO