LYRIC

ነግ በኔ በይ
ኧረ ነገ ነግ በኔ በይ
ምነው
አይበጅሽም አይጠቅምሽም ሀዘኔ
እንደምን ተሳነሽ ማለት ነግ በኔ
አንቺ ቢደርስብሽ የደረሰው በኔ
ምን ይሰማሽ ነበር ብቶኚ እንደኔ
አላሳዝንሽም ወይ እኔ
ምን ብለሽኝ ነበር ያኔ
ልሙትልህ እንዳላልሽኝ
ወይኔ እኔ ከዘመድ አዝማድ ለየሽኝ
አላሳዝንሽም
አላሳዝንም እኔ ወይ
2X
ተይ ተይ ኧረ ተይ
አላሳዝንም ወይ
አሀ ተይ ተይ ተይ
አላሳዝንም ወይ
ይቅርብህ ሲሉኝ ሁሉንም ትቼ
ሁሉንም ትቼ
ከምንም በላ አንቺን አምኜ
አንቺን አይቼ
ከዘመድም ሳልሆን ከጓደኞቼ
ከጓደኞቼ
ከሁለት አንድ ያጣ ሆኜ ቀረሁኝ
ተለያይቼ
ባይተዋር አረግሽኝ ዘመድ አሳጣሽኝ
አላሳዝንሽም ወይ
ማረፊያ እንደሌለው ተንሳፋፊ አረግሽኝ
አላሳዝንሽም ወይ
ግፍ እንደዋልሽብኝ ግፍ ይጠብቅሻል
አላሳዝንሽም ወይ
እንደኔ ተላላ የት ይኖር መስሎሻል
አላሳዝንሽም ወይ
ባንቺ ሁሉን እረስቼ
ዘመድ ጓደኞቼን ትቼ
ከሁለት አንድ ያጣ አረግሽኝ
ወይኔ እኔ ቀረው አንገቴን ደፍቼ
አላሳዝንሽም
አላሳዝንም እኔ ወይ
2X
ተይ ተይ ኧረ ተይ
አላሳዝንም ወይ
አሀ ተይ ተይ ተይ
አላሳዝንም ወይ
ይቅርብህ ሲሉኝ ሁሉንም ትቼ
ሁሉንም ትቼ
ከምንም በላ አንቺን አምኜ
አንቺን አይቼ
ከዘመድም ሳልሆን ከጓደኞቼ
ከጓደኞቼ
ከሁለት አንድ ያጣ ሆኜ ቀረሁኝ
ተለያይቼ
ድንገት ሲያጋጥሙኝ ዘመድ ጓደኞቼ
አላሳዝንሽም ወይ
አቀርቅሬ አልፋለው እንዳላየ አይቼ
አላሳዝንሽም ወይ
ዝናብ ሳያካፋ ጥላ ዘረጋለው
አላሳዝንሽም ወይ
እንደሰረቀ ሰው ተከልዬ አልፋለው
አላሳዝንሽም ወይ
አለሽኝ ስል ተማምኜ
ለካስ ጉም ኖሯል ዘገየን
አስቀረሽኝ ባዶ ሜዳ
ወይኔ እኔ ዘመድ ሁሉ አርጎኝ ባዳ
አላሳዝንሽም
አላሳዝንም እኔ ወይ
2X
ተይ ተይ ኧረ ተይ
አላሳዝንም ወይ
አሀ ተይ ተይ ተይ
አላሳዝንም ወይ
4X

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO