LYRIC

ነገ ሩቅ ነው ኧረ
ሱስ ሆነሽብኝ ወጣጣ
ምስሉ የራቀው ደካማ ነኝ
ሁልጊዜ አንቺን ከአይኔ ሳጣ
ቀን ከለሊት አምጣት ይለኛል
ደሞ የልቤ ነገር ግራ እያለኝ ነው
ሰው እስኪያውቀው ልቤ አንቺን
ነይልኝ ይላል ናፍቆቱን አንግቦ
ገና ስትጠሪ ረጋ አትበይ
ፈጠን ብለሽ ድረሺ ነይ
ቀኔ የሚያምረው ባንቺ ነው ታውቂያለሽ
ስለዚህ ነይ ነይ ነይ አልጣሽ
ሁሌ ከሀሳቤ ነሽ ነሽ ነሽ
ታቂያለሽ ፍጠኝ ቶሎ ድረሽ ድረሽ
ሽቅርቅር እምር ብለሽ
ገና ሲነጋ ሃሳቤ ካንቺ ላይ ነው
መተሽ እርፍ ብል ደስ ቢለኝ ምነው
ሱሴ ነሽና አቅፌ ከጎኔ ታዪ
ምኞቴ ይድረስ ፈጥነሽ ድረሺ ነይ
ልቤ በናፍቆት መምጣት ትቶ
ፍቅርሽ ደንድኖ እኔን ረቶ
ፍግም ብል ምን ይጠቅምሻል
አንቺ ልጅ ስሚ ተይ ይሻልሻል
ስሚ ኩራትሽን ትተሽ ነይ ፈጥነሽ
ነገ ለናፈቀ እሩቅ ነው መሽቶ አይንጋ
ዛሬን አለነው አይኑር በቃ በቃ በቃ
ከአይኔ እርቀሽ ልቤ በአንቺ አይስጋ
ፍቅርን ተሸክሜ ፍቅርን እንዴት እችላለው
ነገሬን ሁሉ መውደድ ላንቺ ሰጥቻለው
አንቺ ብቻ ሆነሽ ለአይን ማራኪ
ፍጹም ይከፋኛል እኔ ከጎኔ ስትርቂ
ስለዚህ ነይልኝ በቶሎ ድረሽ ፈጥነሽ
ዛሬ ሳይገለኝ በርትቷል ፍቅርሽ
ነይ 6X
ደስ

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO