LYRIC

ነይ ነይ ነይ ነይ ወዳጄ ነይ ነይ
ና ና ና ና ወዳጄ ና ና
2x
መጥቻለው ተመቻቺ
ሁሉን ትተሸ ተደሰቺ
ፍቅር ነው ወይ የፈለግሽው
በይ ልብሽን በይ ክፈችው
ልቤ አንቺን ብቻ ነው የሚራበው
ጠዋት ማታ ሁሌም የሚጠማው
ወዳጄ ናት እሷ የምወዳት
እሷን ነው በልቤ ያነገስኳት
ማራኪ ነው ፈገግታዋ
አንበርካኪ ነው ቆንጅናዋ
ፈታ በይ ተጫወች እስኪ ሳቂ
ጠጋ በይ ስቀርብሽ አትራቂ
ያላት ውበት አቤት ይማርካል
ስትጫወት ሁሌም ያምርባታል
ዘና በይ ወዳጄ ተደሰች
መቼም ያላንቺ አይመች
ነይ ነይ ነይ ነይ ወዳጄ ነይ ነይ
ና ና ና ና ወዳጄ ና ና
2x
ፍቅር ነው ያገናኘን
አንቺና እኔን ያተያየን
እንደ ጨረቃዋ አምረሽ መተሽ
ሳላስበው ልቤን ሰረቅሽ
ወይኔ ጉዴ እላለው ወይኔ ጉዴ
በቆንጅናዋ ነው ማበዴ
በድንገት ገብታ ነው አይኔ ላይ
ቤቷን የሰራችው በልቤ ላይ
ከላይ ነው የተሰጣት
የሚያምር ቁመና የሚያምር ውበት
ያያት ሁሉ እንዲወዳት
ሁሉን አሟልቶ ነው የፈጠራት
ልቤ አንቺን ብቻ ነው የመረጠሽ
ውዬ አላውቅም እኔ ሳላስብሽ
ነይ ቶሎ ቶሎ ስናፍቅሽ
ነይልኝ ወዳጄ ስጠብቅሽ

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO