Warning: Creating default object from empty value in /home/ethiolyrics/public_html/wp-content/themes/muusico/framework/admin/ReduxCore/inc/class.redux_filesystem.php on line 29
ነቃሁ – EthioLyrics – Ethiopian Lyrics & Video

LYRIC

እሷ እያለች ሁሌ እኔ አልሰማ
ላንዴ እንኳን ከጎኔ ሄዳ ላትርቅ
እንዴት እንደማዝን ስትርቀኝ
ጥቅሟ ዛሬ ሲጎል ቢታወቀኝ
ነቃሁ ካለቀ
ፍቅሯ ከራቀ
ከአይኔ ስር ሳጣት
ተቀጣሁባት
ወይኔ ወይኔ ወይኔ ብልባት ነው በመሄዷ
ልመልሳት ፈጽሞ አልሞክርም ልቆም በመንገዷ
ስታስረዳኝ ተው ስትለኝ ያኔ ስላልሰማሁ
ይህ ሲያንሰኝ ነው መቼም በሷ አልፈርድም የጄን ስላገኘሁ
ያስለመድሽው ቤጹ ካኮረፈኝ በኔ ፈርዶ
ብዙ ለፋ ግን በምን ሊረሳሽ ጠረንሽን
ብዙ ለፋሁ ትቻት ሆዴን
ብዙ ለፋው አጥቻት ሆዴን
2X
እሷ እያለች ሁሌ እኔ አልሰማ
ላንዴ እንኳን ከጎኔ ሄዳ ላትርቅ
እንዴት እንደማዝን ስትርቀኝ
ጥቅሟ ዛሬ ሲጎል ቢታወቀኝ
ድኖ እንዳልሻረ እንደ እግር እሳት
ያንገበግባል አግኝቶ ማጣት
ወይኔ ወይኔ ወይኔ ማለት ያኔ ሳቴጅ ነበር
ሁሉም አልፎ በናፍቆት በሀሳብ እንዲ ከምሰበር
ምን አቅሜ እንዴት ይለመዳል ያላንቺማ
ሰው ተጣልቶ መኖር እያቃተው ከራስ ሳይስማማ
የኔ እያለች ልቤ ሳይከፍትላት ዘግቶ በሩን
ከየት ትምጣ ዛሬን ቢፈልጋት ሊሰጣት ፍቅሩን
ብዙ ለፋሁ ትቻት ሆዴን
ብዙ ለፋው አጥቻት ሆዴን
2X
ትቻት ሆዴን 2X
አጥቻት ሆዴን 2X
3X

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO