LYRIC

ፍቅርን እወቂበት እወቂበት
መውደድን ቻይበት ቻይበት
በውበት በመልክሽ ኩሪበት
ህይወትሽን በፍቅር ምሪበት
እኔማ ወድጄሽ እጄን ሰጥቻለው
ማፍቀር ዝቅ ማለት መሆኑን አውቃለው
ፍቅርሽ አስገድዶኝ ወደ አንቺ ባደላ
ወደድኩሽ ማለቴን አትይው በሌላ
ሲወዱሽ መውደድን ቻይበት
ልብሽ መወላወል ይቅርበት
ውበትም ይረግፋል በድንገት
እድሜም ያልፋል እኮ እንደዘበት
ቻይበት መላመዱን
ቻይበት ማፍቀሩንም
2X
ቻይበት ቻይበት
ቻይበት መላመዱን
ቻይበት ቻይበት
ቻይበት ማፍቀሩንም
ቻይበት
ፍቅርን እወቂበት እወቂበት
መውደድን ቻይበት ቻይበት
በውበት በመልክሽ ኩሪበት
ህይወትሽን በፍቅር ምሪበት
ልብሽ መረታቱን አምኖ አልተቀበለም
ሰው ማፍቀር ጸጋ እንጂ ሽንፈት እኮ አይደለም
ስቀርብሽ ቅረቢኝ ልብሽ ከቶ አይስጋ
አይከብድም ለፍቅር የሚከፈል ዋጋ
ሲወዱሽ መውደድን ቻይበት
ልብሽ መወላወል ይቅርበት
ውበትም ይረግፋል በድንገት
እድሜም ያልፋል እኮ እንደዘበት
ቻይበት መላመዱን
ቻይበት ማፍቀሩንም
ቻይበት መዋደዱን
ቻይበት ማፍቀሩንም
ቻይበት ቻይበት
ቻይበት መላመዱን
ቻይበት ቻይበት
ቻይበት ማፍቀሩንም
ቻይበት ቻይበት
4X

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO