LYRIC

መቼም አንዴ ተስለሻል ተቀምጠሸል ከሀሳቤ
ብትርቂኝም ሌላ አያይም አይተውሽም ችሎ ልቤ
ሁሌ ስምሽን እያነሳው ትዝታሽን እንዴት ልርሳው 2X
ነይ ነይ እማማዬ ነይልኝ እናትዬ
ነይ ነይ ወዳጄ በይ ነይ ናፍቆቴ
ባልችል እኮ ነው ሳጣሽ ምትናፍቂኝ
ሁሌ ስምሽን አፌ የኒያነሳው
አይደለም እንዲህ እኔስ በቀላሉ
ያንቺን ውለታ ችዬ የምረሳው
ከአንቺ እርቆ በሀሳብ መኖሩን
ሆዴ አልችል ቢለኝ
ይኧው ጮኬ ነይ እልሻለው ብትናፍቂኝ
ስሚኝ እናቴ
ድረሽ በነፍሴ
ብቻ ማደሩ ከበደኝ
ካንቺ መኖሩ ናፈቀኝ
ጎኔ ሁኝልኝ የኔ ጥላ
መራቅሽን ነው የምጠላ
ውብ ፈገግታሽን ተከትሎ
ከልቤ ገብቷል ተከልሎ
ማማዬ ማማዬ 4X
ነይ ነይ ማማዬ
መቼም አንዴ ተስለሻል ተቀምጠሸል ከሀሳቤ
ብትርቂኝም ሌላ አያይም አይተውሽም ችሎ ልቤ
ሁሌ ስምሽን እያነሳው ትዝታሽን እንዴት ልርሳው 2X
ነይ ነይ እማማዬ ነይልኝ እናትዬ
ነይ ነይ ወዳጄ በይ ነይ ናፍቆቴ
እንዴት ይገፋል እስኪ ቀን ለሊቱ
አንቺን አጥቼ ጎኔ አጠገቤ
አለ ሲወድሽ ልቤም እስከዛሬ
ፍቅር ትዝታሽ ዘልቆ ከሀሳቤ
እኔስ ደክሟል አካል አዕምሮዬ
ዝሎልሻል የኔ አለም
ይህን ሰምተሸ ካልመጣሽ ሆዴ
የሚያሽለኝ የለም
ስሚኝ እናቴ
ድረሽ በነፍሴ
ብቻ ማደሩ ከበደኝ
ካንቺ መኖሩ ናፈቀኝ
ጎኔ ሁኝልኝ የኔ ጥላ
መራቅሽን ነው የምጠላ
ውብ ፈገግታሽን ተከትሎ
ከልቤ ገብቷል ተከልሎ
ማማዬ ማማዬ 3X
ነይ ነይ ማማዬ
2X

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO