Warning: Creating default object from empty value in /home/ethiolyrics/public_html/wp-content/themes/muusico/framework/admin/ReduxCore/inc/class.redux_filesystem.php on line 29
ትቅና – EthioLyrics – Ethiopian Lyrics & Video

LYRIC

ትቅና ብለህ ትቅና
ትቅና ብለህ
2x
ልፋትህ ገባ ገደል
ትቅና ስትል ትቅና
ትቅና ስትል
2x
ልፋትህ ገባ ገደል
ተሞኘ ልቤ አመነ የማይታመን
ያለፍኩት ደስታ ሆነብኝ ድንገት ሰመመን
እኩል ሲመስለኝ ፍቅራችን ሚዛን ሳይደፋ
ተሞኘው ባይኔ ኳተንኩኝ በባዶ
ልቤ ነው በዛ ባፈቅርህ ውዴ
እንዲህ እንዲህ አይነት ነገር አለ እንዴ
ከተዋደድን ኋላ በኋላ
ልቅና ልቅና ለማወቅ ገና
ጎዳህ ድርጊትህ ስራህ አመመኝ
ልቅርብህ በቃ አንተም ቅርብኝ
ምን አነሰኝ ጎደለኝ ብዬ
እጣላለው ከአንዱ ጌታዬ
ውብ አድርጎ ለይቶ ሰርቶኝ
ለምን ልቅና ምን አሳጥቶኝ
ብወድህም ብንዋደድም
ሀሳባችን ላይላመድ
አቃቃመኝ ፈተናው ይቅር
ጥሎ ማለፍ አይሻም ፍቅር
ትቅና ብለህ ትቅና
ትቅና ብለህ
2x
ልፋትህ ገባ ገደል
ትቅና ስትል ትቅና
ትቅና ስትል
2x
ልፋትህ ገባ ገደል
ማሩ ከንጉስ ሳይለይ መቼ ይበላል
ምንም ቢጣፍጥ በርቀት ብቻ ይታያል
የማትበላ የማትዋጥ ነህ ከአንጀት
በመላ አትቆይም አትያዝ በብልሀት
ምንም ብወድህ ከማንም በላይ
ባይኔ ባይሞላም ቆንጆ በዝቶ ባይ
እወስናለው ካልሆንከኝ ቅራ
በመቀናናት አይሆንም ፍቅር
መተማመን ነው መፋቀር ለኔ
የሚያሳርፈኝ ቅናት ለምኔ
ብዙ አታስብ አንድ ነው መላው
ንጹህ ፍቅርን ዘዴ ማስቀኛው
ወስንና ቀብረህ ኩራትክን
እንዳታጣኝ የልብ ወዳጅክን
አንድ እንሁን ፍቅር መላ አለው
ላስታዋለ ላወቀበት ሰው
በቃ ተወኝ ፈታነው ይቅር
ጥሎ ማለፍ አይሻም ፍቅር

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO