LYRIC

ተመልሼ ሳይ ተፀፀትኩ ራሴን አወኩና
ካንቺ መለየቱ ቢጎዳኝ የብቸኝነት ጎዳና
አሁን ተረዳው እርቄሽ ሁሉን አወኩና
ባይ ሌላ ሴት…ባይ ሌላ ሴት
አንዳንቺ አልሆን አለኝና(2x)
ካደረግሽው በላይ ያረግሽለት በልጦ
ዛሬም አንቺን ይላል ልቤ ተፀፅቶ
የብቸኝነት ቤት እንዴት ይለመዳል
ከሚወዱት መራቅ ለካ ይከብዳል
እረፍት አጣውና ያንቺን ፍቅር በመራቤ
ባየሺኝ ሰሞኑ ታሞልሻል ልቤ(2x)
ታሞልሻል….ታሞልሻል ልቤ
ታሞልሻል….ታሞልሻል ልቤ(2x)
ተመልሼ ሳይ ተፀፀትኩ ራሴን አወኩና
ካንቺ መለየቱ ቢጎዳኝ የብቸኝነት ጎዳና
አሁን ተረዳው እርቄሽ ሁሉን አወኩና
ባይ ሌላ ሴት…ባይ ሌላ ሴት
አንዳንቺ አልሆን አለኝና(2x)
ይቅርታን የማያምን ልብ አይደለም ሙሉ
የኔም ያንቺም ሲከር ይበጠሳል ውሉ
ከእድሜ ጫፍ አስጠጋኝ ፍቅርሽ ነስቶኝ ጤና
ተይ አኑሪኝ ሁሌም ለአንዴ ማሪኝና
እረፍት አጣውና ያንቺን ፍቅር በመራቤ
ባየሺኝ ሰሞኑ ታሞልሻል ልቤ(2x)
ታሞልሻል….ታሞልሻል ልቤ
ታሞልሻል….ታሞልሻል ልቤ(8x)
ቴዎድሮስ ካሳሁን / ቴዲ አፍሮ/

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO