LYRIC

ጋላቢ ነው ልቤ እንደፈረስ
አዬ ልቤ እንደፈረስ
ችዬም አልቆም ሳላይ ያሰብኩት ሳይደርስ
ህልሜን ሳላይ ሳልደርስ
መንገደኛ እሩቅ አሳቢ
የማልደክም ነኝ ጋላቢ
በል አድርሰኝ ሀሳብ ፈረሴ
በውን ልያት ወታለች ነፍሴ
2X
በውን አድርሰኝ ፈረሴ
አሁን አድርሰኝ ፈረሴ
ህልሜን አሳየኝ ፈረሴ
በውን አድርሰኝ ፈረሴ
የቆረጠው ተጓዥ ልቤ
አንቺን አቶ መች ያርፋል
ምኞት ህልሙን ቸል እያለ
ካለሽበት ይከንፋል
እንዴት በእውን ሳልደርስባት
ናፍቃኝ እሷን ተርቤ
ስከን ቢሉት የት ይቆማል
መንገደኛው ሀሳቤ
ከህልሜ ጋራ እሷም አብራ
በእውን ታስራ
ብክን ብክን መሽቶ እስኪነጋ
ጋላቢ ነኝ ህልሜን ፍለጋ
ከሀሳብ አውጣኝ ሀሳቢ ፈረሴ
በውን አድርሰኝ በነፍሴ
በውን አድርሰኝ ፈረሴ
አሁን አድርሰኝ ፈረሴ
ህልሜን አሳየኝ ፈረሴ
አሁን አድርሰኝ ፈረሴ
በውን አድርሰኝ ፈረሴ
2X
መንገደኛ እሩቅ አሳቢ
የማልደክም ነኝ ጋላቢ
በል አድርሰኝ ሀሳብ ፈረሴ
በውን ልያት ወታለች ነፍሴ
2X
በውን አድርሰኝ ፈረሴ
አሁን አድርሰኝ ፈረሴ
ህልሜን አሳየኝ ፈረሴ
በውን አድርሰኝ ፈረሴ
እራርቶልኝ የፍቅር አምላክ ሳልሞት ባይሽ በነፍሴ
ውቂያኖሱን በሀሳብ እርቆ ይጋልባል ፈረሴ
መዕበል ወጀብ አያስቀረው ፍቅር ያረገው ብርቱ
ተስፋን ይዞ መች ይዝላል ቢፈስ የእድሜ ዥረቱ
ከህልሜ ጋራ እሷም አብራ
በእውን ታስራ
አጠልቅም አጠልቅም ጀምበሯ
ሳላያት ደርሼ ከቀብሯ
ቶሎ አድርሰኝ ናፍቃለች ነፍሴ
በእውን አድርሰኝ ፈረሴ
በውን አድርሰኝ ፈረሴ
አሁን አድርሰኝ ፈረሴ
ህልሜን አሳየኝ ፈረሴ
አሁን አድርሰኝ ፈረሴ
በውን አድርሰኝ ፈረሴ
2X
ትቼ እልም እልም
ሀሳብ እንደው አይገልም
ትቼ እልም እልም
ልቤ አይዝልም አይዝልም
3X

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO