Warning: Creating default object from empty value in /home/ethiolyrics/public_html/wp-content/themes/muusico/framework/admin/ReduxCore/inc/class.redux_filesystem.php on line 29
ተገጣጠሙ – EthioLyrics – Ethiopian Lyrics & Video

LYRIC

አንድ አጥንት ወስዶ ከኔ ግራ
ገረመኝ አንችን ሲሰራ
ስገልጠዉ አይኔን
አየሁሽ ሂዋኔን
ከንፈርሽ ከከንፈሬ
ማር ቀሰሙ ዛሬ
ልብሽ ከልቤ ጋ
ሲሆን ተረጋጋ /2/
የሱን ጥበብ በምን ቃል
ይቻላል ማዉራት
ከኔ ወስዶ ካካሌ
አካሌን ሰራት
ብቸኛ ሁኘ ሲያየኝ
ገና ያኔ
አንችን ሰጠኝ ፈጣሪ
ለኔ ከኔ
ነብሴን ሃሴት ርቋት
እንዳትቀር ሰግታ
ቀኔን ብሩህ አረገዉ
ባንች ፈገግታ
ማረፊያዉን አድሎት
ላይኔ ላይኔ
በፍቅርሽ አስታረቀኝ
እኔን ከኔ
ገና ዛሬ ነዉ መኖር የጀመርኩት
ደስ እያለኝ ፍቅርን ያጣጣምኩት
/አዝማች/

የሂወት ጣም መገኛ
የአዳም ፅናት
የአለምን ስዉር ቅኔ
መፍቻዉ ሂዋን ናት
አሁን ገባኝ ትርጉሙ ገና ዛሬ
ደስተኛ ሁኘ ታየሁ ባንች ፍቅሬ
ልቤ ፍቅር ሲገባዉ ስስት ተማረ
አንችን የኔ የራሴ ማለት ጀመረ
ምን አለ በኛ መሃል
መሞት ባይኖር
ሁሌም መኖር ተመኘሁ
መኖር መኖር
ገና ዛሬ ነዉ መኖር የጀመርኩት
ደስ እያለኝ ፍቅርን ያጣጣምኩት
ከንፈርሽ ከከንፈሬ
ተገጣጠሙ ተገጣጠሙ
ልብሽ ከልቤ ጋር
ተገጣጠሙ ተገጣጠሙ /4/

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO