LYRIC

ምን አይነት ስጦታ ብትታደዪ ነው ወዴ
የማትርቅ የማትሰለቺ ለአይኔ አዲስ የሆንሽ ሁሌ
ከሰው ሁሉ ተለይተሽ አንቺ ብቻ ነሽ በውበትሽ ገዥ
ካንቺ ሆኖ ሁሉ አይከብድሽ
ሃሳቢ መልካም ልበ ውብ ነሽ የኔ
ተውበሻል
የእውነት የእውነት ጸዳል ጌጡን አላብሶሻል
ተውበሻል
እስኪገርመኝ እስኪደንቀኝ
እናቴን መስለሻል
ተውበሻል
መሳይ የለሽ ቆንጅዬ ነሽ
ከውበት በላይ ተውበሻል
ጌጥ አምባር ምን ያስፈልግሻል
ፍቅር አለሽ የማትጠገቢ
ምንትዋብ ለኔ ለኔ ሁኚ
ተውበሻል
የእውነት የእውነት ጸዳል ጌጡን አላብሶሻል
ተውበሻል
እስኪገርመኝ እስኪደንቀኝ
እናቴን መስለሻል
ተውበሻል
መሳይ የለሽ ቆንጅዬ ነሽ
ግርማሽ ደስ ደስ ያለው የተመጣጠነ ውዴ
ከሚገባሽ ልኩ አንዳች ያልጎደለው ውዴ
ከሰው ሁሉ ተለይተሽ
አንቺ ብቻ ልቤ ገብተሽ
ካንቺ ሆኖ ሁሉ አይከብድሽ
ሃሳቢ መልካም ልበ ውብ ነሽ የኔ
ተውበሻል
የእውነት የእውነት ጸዳል ጌጡን አላብሶሻል
ተውበሻል
እስኪገርመኝ እስኪደንቀኝ
እናቴን መስለሻል
ተውበሻል
መሳይ የለሽ ቆንጅዬ ነሽ
ሀበሻት አንቺ የጨዋ ዘር
ፈገግታሽ ያኖረኛል እኔን
ሁሌ አዲስ አዲስ ያረገኛል
ሴትነትሽ ልቤን ገዝቶታል
ከሰው ሁሉ ተለይተሽ
አንቺ ብቻ ልቤ ገብተሽ
ካንቺ ሆኖ ሁሉ አይከብድሽ
ሃሳቢ መልካም ልበ ውብ ነሽ የኔ
ተውበሻል
የእውነት የእውነት ጸዳል ጌጡን አላብሶሻል
ተውበሻል
እስኪገርመኝ እስኪደንቀኝ
እናቴን መስለሻል
ተውበሻል
መሳይ የለሽ ቆንጅዬ ነሽ

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO