LYRIC

እምዬ ጎንደር ጀግና ሀገር 2X
ዛሬም ልጅ አለሽ የሚያስከብር
ሞት የማይፈራ የነ ካሳ ዘር
ካሳን ጥሩልኝ ያን ጀግና ሰው
ቴዲን ጥሩልኝ ያን ጀግና ሰው
ለእናት ሀገሩ የተሰዋው
ቀብራራው ጎንደር ዛሬም ጀግና ነው
ድሮም ቢወዱት ነው በአለም
ጎንደሬ ጀግና ነው እስከ ዛሬ ድረስ
እናት አለም ጎንደር ሁሉም መከታ
እንደ ካሳ ያለ ደግመሽ ውለጅበት
ኮሶውን ቅመም አትጠግብ ጠንስሳው
ቀብራራው ጎንደሬ ዛሬም መራራ ነው
እስኪ ሰው ጥሩ ጀግና ጥሩ
ልክ እንደ ካሳ አሞተ ኩሩ
ተው ተው 4X
አትንኩኝ ባይ ነው ቁጡ እንደ ነብር
አይበገርም ታማኙ ጎንደር
ካሳ ቆራጥ ነው ለሀገር የሞተው
ምድረ እንግሊዝን ያርበተበተው
እጄን ለጠላት አልሰጥም ብሎ
እሳቱን በላው ጮማ አስመስሎ
ተው ተው 4X
ተው ተው ተው ድማማ 4X
በአለም ላይ ይወራል
ጎንደር ክብር ዝናሽ
እሹሩሩሩ ዛሬም ሙሽራ ነሽ
ጀግናን እንደ ጸበል የሚያፈልቀው ሀገር
ከቶ እንደምን ዋለ ሸዋ ጎጃም ጎንደር
እስራሄል ላይ ያለው
እንኳን ጀግናው ህዝብሽ
እናት ሀገር ጎንደር የሁሉም ክብር ነሽ
ድማማ ድማማ 8X
እምዬ ጎንደር ጀግና ሀገር 2X
ዛሬም ልጅ አለሽ የሚያስከብር
ሞት የማይፈራ የነ ካሳ ዘር
ካሳን ጥሩልኝ ያን ጀግና ሰው
ቴዲን ጥሩልኝ ያን ጀግና ሰው
ለእናት ሀገሩ የተሰዋው
ቀብራራው ጎንደር ዛሬም ጀግና ነው
ሲወድ ወለላ ነው ሲጠላም እንደዛው
ላመነበት ሟች ነው ታማኝ ነው ጎንደሬ
እስቲ ልነሳና ፋሲል ግንቡን ልዙር
መቼም ጀግና አላጣም የነ ቴዎድሮስ ዘር
ቅንነት ጀግንንት ለጎንደር ታዘዘ
ቴዲ ተሰውቷል ኢትዮጵያን እያለ
እስኪ ሰው ጥሩ ጀግና ጥሩ
ልክ እንደ ካሳ አሞተ ኩሩ
ተው ተው 4X
የአበቄለሽ ልጅ የነ ገብሬ ዘር
ታማኝ አይከዳም ቀብራራ ጎንደር
ጀግናው ጎንደሬ ካሳ ቆራጡ
አንገዛም ባይ ባለ አንደበቱ
ጠላት አግቶ መድፍ ያሰራው ሰው
ነዋይ ጠባቡ ጀግናው በይሰው
ተው ተው 4X
ተው ተው ድማማ 4X
በፍቅር ነው እንጂ
ለሰው የዋህ ጎንደር
ሲነኩት አይወድም የነ ቴዎድሮስ ዘር
የአጼ ፋሲለደስ አሻራ ያለብሽ
ጎንደር ጎንደር ሲባል ያኮራል ክብርሽ
ዘውድሽን ልበሽው ካባሽን ደርበሽ
ሙሽራይቱ ጎንደር የታለ ሰርገኛሽ
ድማማ ድማማ 8X

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO