LYRIC

የተለያየን እለት ልቤ አዝኖ ሊከፋ
ምወዳት ከልቤ ነበረ በተስፋ
ስትሰናበተኝ ላይቀር መተከዜ
ሰው አልሰማ እያልኩኝ በፍቅሯ መያዜ
ይኧው ዛሬ ስትሄድ ሆዴ ባባ
ተናነቀኝ ተናነቀኝ እንባ
2X
ሰው ንቄ አታውራት ተው ሲለኝ ያኔ 4X
ያኔ ሲነግረኝ ሰው ፈርቶ
አኳሀኗን አይቶ
ለኔ እንደማትሆነኝ አልሰማም አልኩና
ስትሄድ ሆዴ ባባ ተናነቀኝ ተናነቀኝ እንባ
2X
ሰው ንቄ አታውራት ተው ሲለኝ ያኔ 4X
ለስንት ያሉት ፍቅር በጅምሩ ሲቀር
ምን አማራጭ አለኝ ከመቀበል በቀር
ልሰናበት ብዬ ሳወጋት ቀርቤ
ይጨነቅ ጀመረ የሚወዳት ልቤ
እንቢ አለ ሆዴ ካለሷ
እግሯ ሊሄድ ሲነሳ
አፏ እንቢ ሲል ግን ማልዴ
ሰው ይገርማል ግን አንዳንዴ
2X
ተናነቀኝ
ሰው ንቄ አታውራት ተው ሲለኝ ያኔ 4X
ቃሏን አምኜ ስቀርባት
መስሎኝ የማላጣት
ይህ ሳይመጣ ገና
አልሰማም አልኩና
ስትሄድ ሆዴ ባባ
ተናነቀኝ ተናነቀኝ እንባ
2X
እሪ በከንቱ ልል ዛሬ
ትናንት ስትሄድ ፍቅሬ
ይህ ሳይመጣ ገና
አልሰማም አልኩና
ስትሄድ ሆዴ ባባ
ተናነቀኝ ተናነቀኝ እንባ
2X
ሰው ንቄ አታውራት ተው ሲለኝ ያኔ 4X
ሰው የፈራው ደርሶ
ሀዘን ልቤን ወርሶ
ተለይታኝ ስትሄድ ተናነቀኝ ለቅሶ
ልሰናበት ብዬ ሳወጋት ቀርቤ
ይጨነቅ ጀመረ የሚወዳት ልቤ
እንቢ አለ ሆዴ ካለሷ
እግሯ ሊሄድ ሲነሳ
አፏ እንቢ ሲል ግን ማልዴ
ሰው ይገርማል ግን አንዳንዴ
ለካ ላፍቃሪው ነው መርዶ
ሲለያዩ ተላምዶ
አፏ ኪዳንን ሻረ እንዴ
ቃል እንደዚ ሆነ እንዴ
ግን እንዲህ ሆነ እንዴ
ቃል እንዲህ ሆነ እንዴ
2X

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO