LYRIC

ፍቅር ውስጤ ነዶ ልቤ ተቀጣጥሏል
ክፉህን እንዳላደርግ ያስጥለኛል
ሴት ጠላው ስትለኝ መሸሽ እያማረኝ
መልሼ መጣለው ሱስህ እያሮጠኝ
ቃል ሲወጣ ከአፍህ እኔ እታመማለው
ይለወጣል ብዬ ልቤን አሞኛለው
ይሄ ሞኝ ልቤ በተስፋ ይስቃል
የለመደህ አይኔ አንተን ይጠብቃል
ተመከር ተመከር 4X
ልቤ ሞኝ ነው ያመነኛል
ትንሽ ጠብቂው ይለኛል
እራሴን ስዋሽ ከርሜ
እውነት እውነቱ ይጥመኛል
2X
ፍቅር ውስጤ ነዶ ልቤ ተቀጣጥሏል
ክፉህን እንዳላደርግ ያስጥለኛል
ሴት ጠላው ስትለኝ መሸሽ እያማረኝ
መልሼ መጣለው ሱስህ እያሮጠኝ
አትራቀኝ ይቅር አይንህ ይሻለኛል
ሰነፍ አንደበትህ መች ያባብለኛል
መቁረጥህን እስካይ እኔ እታገሳለው
ከሆዴ ገብተሀል ምን አደርግሀለው
ተመከር ተመከር 4X
ይሆናል ብዬ ልበርታ
ብዙ ያሳያል ቆይታ
በቀና ታየኝ ይሆናል
በቀኝህ የነቃህ ለታ
ተመከር ተመከር 8X

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO