LYRIC

ባገር ማማሩን ማን አቶ
ወልዶ መሳምን ማን ጠልቶ
ችግር ነው እንጂ ፈተናው
ቅርቡን እሩቁን ያስመኘው
2X
ተመቺኝ 2X
ሀገሬ ተመቺኝ
4X
እንባ ባይኔ ላይ ሲመራ
በጉንጬ መሀል ተዘራ
የቱንም ያህል አንብቼ
ለቅሶ መፍትሄ ላይሆነኝ
ትናንትናን ግን አስታውሶ
አሁን አሁን አመመኝ
አስኮብልሎ በመሸከም ጥላሽን
ደህና አድርጎ ቢያስለፋኝ
ሆዴም እኮ ቢሆን ባዳ
መቼም አልሆን ለሀገሬ እንግዳ
እጄ ሊይዝ ሲል አጣሽ
እኔ በኛ እየተቀጠፍሽ
ፈገግታ አቶ ምን ቢጣራ
አስባለው ዘመን ዘመን
አልጠላሽም 4X
ባገር ማማሩን ማን አቶ
ወልዶ መሳምን ማን ጠልቶ
ችግር ነው እንጂ ፈተናው
ቅርቡን እሩቁን ያስመኘው
2X
ተመቺኝ 2X
ሀገሬ ተመቺኝ
4X
ሆዴ ቢረበሽ እንካ አቶ
ሀሳብ ቢገፋኝ አውጥቶ
ሰውነት ዝሎ ቢሳነፍ
ነፍሴም ፈለገች ለመትረፍ
ሺ ጥጋብ እድሜን ሳይገዛ
ቅምሻ መሰንበት ባይረባ
ሀሳብ ያጣውን አሳስሮ
ሆዴ ሆዴን አባባ
በሰላምሽ እንድረጋ
በተፈጥሮሽ እንድፈካ
ሚያስቆጣኝን ፍቅር ቀጥፈሽ
የራበኝን ሳልነግርሽ
በናፈኩት የእናት ፍቅር
እሱን ከምል ከኔ ሆነሽ
ከአህዋፎች ጋር አዛመድሽኝ
እማ ሀገሬ ተይ ታረቂኝ
አልጠላሽም 4X
እናቴ እኮ ነሽ
አልጠላሽም 2X
ልቤ
አሁን ይጸዳ
ሰዉን ከኑሮ
እንዲ እያጉላላ
የሀገሬው አምላክ ባክህ ጠብቀን
በያለንበት አሜን ሰባስበን

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO