LYRIC

ኧረ ተው አምጡልኝ በሬ
በዲማው ጊዮርጊስ የአባ ኮስትር በላይ
ገድሎ አንጀት ለኔ የሚያርስ
ሀገሩ በጣሊያን ተይዞ ወገን ሲታመስ
ለሊት ለምቸ ማርያም ታግሎ በበነጋው ማርቆስ
በሩቅ ዱላ ታዲያ በጭስ ቦምብ ቢያስቸግር
አይ አተኳኮስ እናቴዋ አይ አገዳደል
ልክ እንደ ወስኬ አልሞ መራሹን መንደል ብሎ መራ እቴዋ
በዛ በደሽር በዛ ከርካሳ
በአንድ እጁ ጥይት በአንድ እጁ ካርታ
የዘለቀ ልጅ የወንዶች ቁና
ውሻውን አንጋሎ የሚኖር በድል
አንበሳው ኮስትር በለው ያለ ለት
ጎጃሜው ጦሩነረ የሰበቀው ለት
ምን አለ ሰማይ ምን አለ መሬት
የዛን ጊዜ ነው ጀግናው ማየት
አስጨናቂ ነው የማንድ አርበኛ
የማያስቀምጥ የማያስተኛ
ቢሼ ላይ ሆኖ ኮስትር ሲያስካካ
የወንዱን እናት ግን ማነው የሚነካ
ኧረ ማነው ጀግና
አባይን የሚሻገር
ይሞክረው ክንዱን
ከፊላእሸቱ ስር
ቆራጥ ጀግና ለጦር
እሺ የማይመክተው
እንደ ጣናው ጎንደር
ወስዶ የሚያላትመው
ከስር ድማሚቱን
እያነደደው
ከትከት ብሎ ሳቀ
ኮስትር ምን አለበት
ኧረ ተው አምጡልኝ ወኔ
በዲማው ጊዮርጊስ
የአባ ኮስትር በላይ
ገድሎ አንጀት ነው የሚያርስ
ነጋሪት ሲቦሰም ክለት
ሲነፋ ገምባው
አለሁለህ ይለው ነበር እያበጀ ጋሜውን
አመጣው ምን እሽር ታዲያ
ባመጣው ጥይት
ያስጨንቀው ነበር ወንዱ ቀን እና ለሊት
ቢሻናና ደጀን ነብሱን እናርጅና እናውጋ
ማንን ተክታችሁ ይሆን
በዛ በደሽር በዛ ከርካሳ
በአንድ እጁ ጥይት በአንድ እጁ ካርታ
የዘለቀ ልጅ የወንዶች ቁና
ሻውን አንጋሎ የሚኖር በድል
አንበሳው ኮስትር በለው ያለ ለት
ጎጃሜው ጦሩነረ የሰበቀው ለት
ምን አለ ሰማይ ምን አለ መሬት
የዛን ጊዜ ነው ጀግናው ማየት
አስጨናቂ ነው የማንድ አርበኛ
የማያስቀምጥ የማያስተኛ
ቢሼ ላይ ሆኖ ኮስትር ሲያስካካ
የወንዱን እናት ግን ማነው የሚነካ
ኧረ ማነው ጀግና
አባይን የሚሻገር
የሚሞክረው ክንዱን
ከፊላእሸቱ ስር
ቆራጥ ጀግና ለጦር
እሺ የማይመክተው
እንደ ጣናው ጎንደር
ወስዶ የሚያላትመው
ከስር ድማሚቱን
እያነደደው
ከትከት ብሎ ሳቀ
ኮስትር ምን አለበት
ኧረ ተው አምጡልኝ ወኔ
በዲማው ጊዮርጊስ
የአባ ኮስትር በላይ

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO