LYRIC

ባያት ባያት ባያት
በሄድኩበት ባለፍኩበት ቦታ
ባያት ባያት ባያት
አትሰለቸኝ አልጠግባትም ለአፍታ
ትታጥ ትውጣ ትታይ
የኔ ቆንጆ እንደ ጸሀይ ፈክታ
ባያት ባያት ባያት
አትሰለቸኝ አልጠግባትም ለአፍታ
ቆንጆ ናት ቆንጆ ቆንጆ 4X
ቆንጆ 2X
እንዴት ብዬ እሄዳለው
ሁሌ አስታውሳለው
ቀን በቀን በሀሳቤ መች እረሳሻለው
እልፍ ብዬ እሄዳለው
ደሞ እመለሳለው
ቀን በቀን በደጅሽ እመላለሳለው
አንዴ አንዴ ነይ እስኪ እናውጋ
በፍቅር በኩል ነይ በተስፋ
አንቺን አንቺን ልቤ የሚለው
ፍቅር ነው
የፍቅር ልቡ የተለየ
ሲፈልግ ውሎ ይላል አንቺን ያየ
አንቺን አንቺን ልቤ የሚለው
ፍቅር ነው
ቆንጆ ናት ቆንጆ ቆንጆ 4X
ቆንጆ 2X
ውበትሽ ማራኪ የኔ ውብ አማላይ
ደምግባት ቆንጅና ሁሉን ሰቶሽ ከላይ
የኔ ላርግሽ የኔ
ፍቅሬ ውብ አለሜ
አትፍሪ አትራቂ ሁሌ ሁኚ ጎኔ
አንዴ አንዴ ነይ እስኪ እናውጋ
በፍቅር በኩል ነይ በተስፋ
አንቺን አንቺን ልቤ የሚለው
ፍቅር ነው
የፍቅር ልቡ የተለየ
ሲፈልግ ውሎ ይላል አንቺን ያየ
አንቺን አንቺን ልቤ የሚለው
ፍቅር ነው
ቆንጆ 4X

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO