LYRIC

ቆንጆ ናት
ቆንጆ ቆንጆ ቆንጆ ናት
ቆንጆ ናት
የኔ ቆንጆ ቆንጆ ናት
4X
የልቤ ቃና ነሽ የደሜ መዘውር
የፈገግታዬ ምንጭ የህይወቴ ሚስጥር
ገዝቶኛል ጸባይሽ ስነምግባርሽ
ውበት ደምግብትሽ ማር አንደበትሽ
እንቅልፍ አይወስደኝም በአይኔ ተስለሻል
የልቤን ከተማ በፍቅርሽ ገዝተሻል
ፍልቅልቅ ይበሉ ጥርሶችሽ ያምራሉ
የአይኖችሽ ቀለም ኦ ልብ ይሰውራሉ
እስቲ አቆለባብሽው ከል ካለ ልቤ
ናር ናር ትበል ታዝናናው መንፈሴ
ፍቅርሽ አዲስ ይሁን በነጋ በጠባ
ደስታና ፌሽታ በደማችን ይግባ
ይግባ 3X
ከመልክ ከቁመና አሟልቶ የሰጣት
ደስ ይበለው ልቤ በውበትሽ ፍካት
ይዘምር ይደንስ ይፈንጥዝ ይደሰት ይግባ
ይግባ
ቆንጆ ናት
ቆንጆ ቆንጆ ቆንጆ ናት
ቆንጆ ናት
የኔ ቆንጆ ቆንጆ ናት
4X
ግሩም ትህትናሽ መልካም ሰላምታሽ
አምሳያ የለውም ውበት ጸባይሽ
ጸባይ ከውበት ጋር አሟልተሽ ይዘሻል
በልቤ ውስጥ ገብተሽ ባይኔ ታትመሻል
የአይንሽ ሽፋሽፍት ግሩም ፈገግታሽ
አለንጋው ጣቶችሽ ዞማው ጸጉርሽ
የወገብሽ ቅጥነት ሰንደዶ አፍንጫሽ
የተጎጀ ጡትሽ አረማመድሽ
ለኔ ተፈጥረዋል የአለም ቆንጆ ነሽ
የፍቅር አድባር ነሽ የውበት እመቤት
በልቤ ከተማ ዋዪ እደሪበት
ቆንጆ ልጅ ናት እሷ ከልቤ የገባች
በደሜ ስር ገብታ መንፈሴን የገዛች
በፍቅር አጡዛ ልቤን የማረከች
የማንም ሳትሆን ለእኔ ቆንጆ እሷ ብቻ ነች
ነች ነች
ቆንጆ ናት
ቆንጆ ቆንጆ ቆንጆ ናት
ቆንጆ ናት
የኔ ቆንጆ ቆንጆ ናት
4X
ቆንጆ ናት 3X
ቆንጆ ቆንጆ ቆንጆ ናት

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO