LYRIC

ቀን ወጥቶ የጨለመው ነግቶ
ከመሬት አንስቶ አንቺን ለኔ ሰጥቶ
አስጫነኝ እጄንም አፌ ላይ
እንዲሽር ስሜቴ አኖረሽ ከቤቴ
ወግ አየሁኝ በቃ የኔ ሴት ነሽ ለካ አ አ አ አ… 2×
ያሰብኩት ሌላ ነው ህልምና ምኞቴ
ግን ፍቅር አመጣሽ ከደሳሳው ቤቴ
ለካስ ሰው አልሞ ፍቺውን አይኖርም
ነገም እንደዛሬ ከቶ አይሆንም
ከዘፍጥረት አለም ይኧው እስከዛሬ
ፍቅርና ጥላቻ ተግባርና ወሬ
ልቤ ሌላ ሲያስብ አይኖቼ አማትሮ
ለካ አንቺ ሆነሻል የኔ ሴት ወይዘሮ ሮሮ…..
የኔኔኔ…ሴት ወይዘሮ
ኦ ኦ ኦ ኦ ኦ ኦ የኔ ሴት ወይዘሮ…
የኔ ሴት ወይዘሮ…2×
ቀን ወጥቶ የጨለመው ነግቶ
ከመሬት አንስቶ አንቺን ለኔ ሰጥቶ
አስጫነኝ እጄንም አፌ ላይ
እንዲሽር ስሜቴ አኖረሽ ከቤቴ
ወግ አየሁኝ በቃ የኔ ሴት ነሽ ለካ አ አ አ አ… 2×
አለም ሳይፈጠር ለኔ ታስበሽ
ከጎበዞች መዳፍ ይኧው አስጣለሽ
ወለል ብሎ ታየኝ ቀኝ እና ግራዬ
በምድር እስካለው ነሽ ድርሻዬ
ለካ ይታደላል ሰው ሰው እንደአመሉ
መቀበል ነው እንጂ ዋናው ቁም ነገሩ
ልቤ ሌላ ሲያስብ አይኖቼ አማትሮ
ለካ አንቺ ሆነሻል የኔ ሴት ወይዘሮ ሮሮ…..
የኔኔኔ…ሴት ወይዘሮ
ኦ ኦ ኦ ኦ ኦ ኦ የኔ ሴት ወይዘሮ…
የኔ ሴት ወይዘሮ…2×

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO