LYRIC

ሼመንደፍር
አሆ..አሆ..ሼመንደፍር
ሼመንደፍር ሼመንደፍር
አሆ..አሆ..አሆ..አሆ.. ሼመንደፍር
ሼመንደፍር ሼመንደፍር
አዛን አለ መስጅድ ፣ ልት ነጋ ምድር
ልሒድ ሼመንደፍር ፣ ልሳፈር ባቡር
በንግድነት መ’ታ ፣ ከሸገር ሀረር
ልቤን ይዛው ሄደች ፣ ወደ ሩቅ ሀገር
/ሼመንደፍር/
ተዋዶ ያለበት ፣ እስላም ክርስቲያኑ
ተዘነጋሽ እንዴ ፣ ኢትዮጵያ መሆኑ
አንቺም ባይማኖትሽ ፣ እኔም ባይማኖቴ
መኖር እንችላለን ፣ አይጠበንም ቤቴ
/ሼመንደፍር/
ውብ አርጎ ቢሰራሽ ፣ የሰማይ ፈጣሪ
አይደል ሰው እንድትቀይ ፣ የአላህን ሳትፈሪ
ሲወዱሽ አታውቂ ፣ ወይ እሺ አትይ እምቢ
አረ..ያንቺስ ለጉድ ነው ፣ ያንተ ያለህ
ያንቺስ ለጉድ ነው ፣ ያንተ ያለህ
ሸመንደፍር
አድርሰኝ ባቡሩ ፣ ፈጥነህ ለሃዲዱ ሸገር
አልችልምና መቸገር ፣ አልችልምና መቸገር
አሆ..አሆ..አሆ.. ሼመንደፍር
አሆ..አሆ..አሆ.. ሼመንደፍር
እኔ ሀገሬ ሀረር ፣ ትውልዴ ቁልቢ
ንግስ ብለሽ መ’ተሽ ፣ ከልቤ ብትገቢ
ካልወጣው ካስርቱ ፣ ከሲፈቱ ስፍታ
አንቺን በመውደዴ ፣ አይቆጣም ጌታ
/ሼመንደፍር/
ሸገር አዲሳባ ፣ አንቺ ያለሽበት
እራጉኤል አይደለም ፣ የአንዋር ጎረቤት
ቅዳሴና አዛኑን ፣ አጥር ቢለያቸው
ፈጣሪ ከሰማይ ፣ አንድነት ሰማቸው
/ሼመንደፍር/
እኔ ልማል በላህ ፣ አንቺም በቁልቢ
ክርሽን ሳትፈቺው ፣ ነይ ከቤቴ ግቢ
ሲወዱሽ አታውቂ ፣ ወይ እሺ አትይ እምቢ
አረ..ያንቺስ ለጉድ ነው ፣ ያንተ ያለህ
ያንቺስ ለጉድ ነው ፣ ያንተ ያለህ
ሸመንደፍር
አድርሰኝ ባቡሩ ፣ ፈጥነህ ለሃዲዱ ሸገር
አልችልምና መቸገር ፣ አልችልምና መቸገር
አሆ..አሆ..አሆ..አሆ.. ሼመ.ንደፍ.ር
አሆ..አሆ..አሆ..አሆ.. ሸመንደፍር

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO