Warning: Creating default object from empty value in /home/ethiolyrics/public_html/wp-content/themes/muusico/framework/admin/ReduxCore/inc/class.redux_filesystem.php on line 29
ስደቴን አታስታውሰኝ – EthioLyrics – Ethiopian Lyrics & Video

LYRIC

ህይወት ብላኝ አልቀናኝ
ሳዝን የምታጽናናኝ
አንተ መልካም ወገኔ
ዛሬ ተርቤህ ላይኔ
ዋ እኔ እያልኩኝ እንዳልቀር
ሆዴን ሆድ እየባሰኝ
ስደቴን አታስታውሰኝ
2X
ቢሳካ ቢሞላ ነገሩ
ማን መኖር ይጠላል ባገሩ
አይዞህ በለኝ እንጂ በርታልኝ
ስደቴን አታንሳው ተውልኝ
አትበልኝ ተመለስ
ተስፋዬን ፍለጋ ወጥቼ
አልመጣም ያለኝን አጥቼ
ያሰብኩት ሞልቶ እስኪመልሰኝ
በርታ እንደል ብርታትክን አውሰኝ
ስደቴን አታስታውሰኝ
ልታበዛው ብሶቴን
አታስታውሰኝ ስደቴን
የወጠንኩት እስኪደርስ
አትበልኝ ተመለስ
ገላዬ እንጂ እሩቅ የሆነው
ልቤማ ዛሬም በሀገሬ ነው
ፈጣሪ ፈቅዶ እስኪመልሰኝ
ስደቴን ባክህ አታስታውሰኝ
ገላዬ እንጂ እሩቅ የሆነው
ልቤማ ዛሬም በሀገሬ ነው
ፈጣሪ ፈቅዶ እስኪመልሰኝ
ስደቴን ባክህ አታስታውሰኝ
ህይወት ብላኝ አልቀናኝ
ሳዝን የምታጽናናኝ
አንተ መልካም ወገኔ
ዛሬ ተርቤህ ላይኔ
ዋ እኔ እያልኩኝ እንዳልቀር
ሆዴን ሆድ እየባሰኝ
ስደቴን አታስታውሰኝ
2X
ለይምሰል ሳቅ ቢልም ጥርሴ
ከፍቷታል ስደተኛ ነፍሴ
ልመልስ የሆዴን ጥያቄ
ከሀገር ከወገኔ እርቄ
ያሰብኩት አልሆንም ብሎኛል
ከነፍሴም ከኪሴም ጎሎኛል
እያየሁ እንድኖር የፊቴን
ተወኝ አታንሳብኝ ስደቴን
ልታበዛው ብሶቴን
አታስታውሰኝ ስደቴን
የወጠንኩት እስኪደርስ
አትበልኝ ተመለስ
ገላዬ እንጂ እሩቅ የሆነው
ልቤማ ዛሬም በሀገሬ ነው
ፈጣሪ ፈቅዶ እስኪመልሰኝ
ስደቴን ባክህ አታስታውሰኝ
4X

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO